ደስታ ፡ ለዓለም (Desta Lealem) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Lyrics.jpg


(3)

የምስራቹ ፡ ቃል
(Yemeserachu Qal)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 3:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

ደስታ ፡ ለዓለም ፡ ጌታ ፡ መጥቷል
ምድር ፡ ተቀበዪው
ልባችሁን ፡ አዘጋጁ ፡ ሰማይና ፡ ምድር
በአንድነት ፡ ዘምሩ
መዝሙር ፡ መዝሙር ፡ ለህጻኑ

ደስታ ፡ ለዓለም ፡ አዳኝ ፡ ነግሷል
ሰዎች ፡ ዘምሩለት
የዓለም ፡ ሜዳ ፡ ተራራውም ፡ ደስታውን ፡ ይናገር
ምድርም ፡ ትደሰት
ምድር ፡ ምድርም ፡ ትደሰት

ኃጢአት ፡ ይጥፋ ፡ ሃዘን ፡ ይራቅ
ምድርም ፡ ከእሾህ ፡ ትረፍ
በረከቱን ፡ ሊያፈስ ፡ መጥቷል
መርገምንም ፡ ሊሽር (፪x)
መርገም ፡ መርገምንም ፡ ሊሽር

የዓለም ፡ ገዢ ፡ ጻድቅ ፡ ፈራጅ
ሕዝቡን ፡ ሊያገለግል
የክብሩን ፡ ኃይል ፡ የጽድቁን ፡ ምንጭ
ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ወርዷል (፪x)
ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ከላይ ፡ ወርዷል