የመቶ ፡ አለቃው ፡ መዝሙር (Yemeto Aleqaw Mezmur) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Mekrez Youth Ministry 4.jpeg


(4)

አየዋለሁ ፡ መስቀሉን
(Ayewalehu Mesqelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

የኀጢአትን ፡ ጉልበት ፡ በሞቱ ፡ ሲሰብር
ይህን ፡ ጊዜ ፡ ተረዳሁ ፡ ጻድቅ ፡ እንደነበር
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ነፍሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ
የፍቅሩን ፡ ልክ ፡ አየሁ ፡ አመንኩበት ፡ ያኔ

አዝ፦ እንዲህ ፡ የወደደኝ ፡ ሳልወደው
ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

የእኔን ፡ ሃፍረት ፡ ሊከድን ፡ ራቁቱን ፡ ሲሰቀል
አየእኔ ፡ አይታዋለች ፡ ቅጣቴን ፡ ሲቀበል
ጻድቅ ፡ ሆኖ ፡ ሳለ ፡ ሕይወቱን ፡ የሰጠው
የፍቅር ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ ቢወደኝ ፡ ነው

አዝ፦ እንዲህ ፡ የወደደኝ ፡ ሳልወደው
ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

እኔን ፡ ለመታደግ ፡ ስቃዬን ፡ ሲቀበል
ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ልበል
የሾህ ፡ አክሊል ፡ ደፍቶ ፡ ሲቆስል ፡ ሲደፋ
አምኜ ፡ ተናገርኩ ፡ ፍጥረት ፡ ይህን ፡ ይስማ

አዝ፦ እንዲህ ፡ የወደደኝ ፡ ሳልወደው
ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ እንዲህ ፡ የወደደኝ ፡ ሳልወደው
ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፭x)