ወድሃለሁ (Wedehalehu) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Mekrez Youth Ministry 4.jpeg


(4)

አየዋለሁ ፡ መስቀሉን
(Ayewalehu Mesqelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ወደአንተ ፡ ጮህኩኝ
ድምጼንም ፡ አድምጠህ ፡ ፊትም ፡ መለስክልኝ
እግሮቼንም ፡ አጸናህ ፡ እንዳልወድቅ ፡ ደገፍከኝ
ተመስገን (፪x)

ከብዙ ፡ ጥልቅ ፡ ውሃም ፡ በእጅህ ፡ አወጣኀኝ
ከብርቱ ፡ ጠላቶቼ ፡ ነጥቀህ ፡ አስመለጥከኝ
በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ሃይሌ ፡ ሆንክልኝ
ተመስገን (፪x)

አዝወድሃለሁ ፡ በሙሉ ፡ ልቤ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድሃኒቴ
አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ወድሃለሁ
ሁሁሁሁ (፪x)

አንተ ፡ ጨለማዬን ፡ ብርሃን ፡ ታደርጋለህ
የተዘጋውን ፡ ቅጥር ፡ ታዘልለእኛለህ
መጠጊያ ፡ ለሚያደርጉህ ፡ ጋሻ ፡ ትሆናለህ
ተመስገን (፪x)

አዝወድሃለሁ ፡ በሙሉ ፡ ልቤ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ አምባ ፡ መድሃኒቴ
አቤቱ ፡ ጉልበቴ ፡ ወድሃለሁ
ሁሁሁሁ (፫x)