አየዋለሁ ፡ መስቀሉን (Ayewalehu Mesqelun) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Mekrez Youth Ministry 4.jpeg


(4)

አየዋለሁ ፡ መስቀሉን
(Ayewalehu Mesqelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

 
በእግዚአብሔር ፡ መልክ ፡ ሲኖር ፡ ሳለ ፡ ራሱን ፡ አዋረደ
የህ ፡ ህማም ፡ ሰው ፡ በደዌ ፡ ደቀቀ
ሆኖ ፡ ተቆጠረ ፡ ሞቴን ፡ በሞቱ ፡ ሻረ
መድህኔ

በሸላቾቹ ፡ ፊት ፡ ዝም ፡ እንደሚል ፡ ጠቦት
ተረዳ ፡ ወደሞት ፡ አምላክ ፡ ፍቅር ፡ ይዞት
በኀጢአቴ ፡ ፈንታ ፡ ሆነልኝ ፡ ይቅርታ
መድህኔ

አዝ፦ አየዋለሁ ፡ መስቀሉን ፡ አልረሳውም ፡ ፍቅሩን
ለእኔ ፡ የከፈለው ፡ ዋጋ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው
መቼም ፡ አይፈጠር ፡ ከዚህ ፡ ሚበልጥ ፡ ፍቅር (፪x)
አልረሳውም ፡ ፍቅሩን (፪x)

ተፈጸመ ፡ ዓለም ፡ የአዳም ፡ ልጅ ፡ ስቃይ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ጨልጦት ፡ ጿውን
ሞቴን ፡ በሞቱ ፡ ሻረ ፡ እዳዬንም ፡ ከፈለ

አዝ፦ አየዋለሁ ፡ መስቀሉን ፡ አልረሳውም ፡ ፍቅሩን
ለእኔ ፡ የከፈለው ፡ ዋጋ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው
መቼም ፡ አይፈጠር ፡ ከዚህ ፡ ሚበልጥ ፡ ፍቅር (፪x)
አልረሳውም ፡ ፍቅሩን (፪x)