አማኑኤል (Amanuel) - መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት
(Mekrez Youth Ministry)

Mekrez Youth Ministry 4.jpeg


(4)

አየዋለሁ ፡ መስቀሉን
(Ayewalehu Mesqelun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመቅረዝ ፡ የወጣቶች ፡ አገልግሎት ፡ አልበሞች
(Albums by Mekrez Youth Ministry)

"ለተቀበሉት ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ በሥሙ ፡ ለሚያምኑት
ለእነርሱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ይሆን ፡ ዘንድ
ስልጣንን ፡ ሰጣቸው ።
የእግዚአብሄርን ፡ ስጦታ ፡ ኢየሱስን ፡ እንቀበል ።"

በመጀመሪያ ፡ ቃልም ፡ ነበር
ቃልም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ
ቃልም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
ቃልብ ፡ በእግዚአብሄ ፡ ዘንድ
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ (ሆነ)
ፀጋን ፡ እውነትን ፡ ተሞልቶ
በእኛ ፡ አደረ ፡ እንደ ፡ እኛ ፡ ሰው ፡ ሆነ

አዝአማኑኤል (አማኑኤል) ፡ አማኑኤል (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው
አማኑእኤል

በጨለማ ፡ የነበርን ፡ የንጋት ፡ ፀሃይ ፡ ወጣልን
በሞት ፡ ጥላም ፡ የነበርን ፡ የሕይወት ፡ ብርሃንን ፡ አየን
ብርሃን ፡ ሆነ (ሆነ) (ቃል ፡ ተቀበልን) ፡ ሆነ
ከአባቱ ፡ ዘንድ ፡ የሆነውን (ኢየሱስን ፡ አየን)
አንድ ፡ ልጁን ፡ አየን (አማኑኤል)

አዝአማኑኤል (አማኑኤል) ፡ አማኑኤል (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው
አማኑእኤል (፪x)