From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንዳሳቡ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ
እንዲደረግ ፡ እናውቃለን (፪x) [1]
እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንዳሳቡም ፡ ለተጠሩ ፡ አሄ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው (፪x)
በዚጌውም ፡ አለጊዜው
ሊከብርብን ፡ የሚገባው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዚጌውም ፡ አለጊዜው
ሊነግስብን ፡ የሚገባው ፡ ኢየሱሴ ፡ ነው
ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለሁሉም ፡ ነገር
ለሁሉም ፡ ቀን ፡ አለው
ለሁሉም (ለሁሉም ፡ ቀን ፡ አለው) (፪x)
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንዳሳቡ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ
እንዲደረግ ፡ እናውቃለን (፪x) [1]
ነገሬን ፡ ሁሉ ፡ በዚጌው ፡ ውብ ፡ አድርጐ ፡ ሰራ
ከተሰራልኝ ፡ ነገር ፡ ለእኔስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)
ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው
ለሁሉም ፡ ነገር
ለሁሉም ፡ ቀን ፡ አለው
ለሁሉም (ለሁሉም ፡ ቀን ፡ አለው/ነገር) (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ይክብር ፡ እንጂ ፡ በሕይወቴ
ሌላው ፡ ሌላው ፡ ይሆናል ፡ አለው ፡ ጊዜው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይንገሥ ፡ እንጂ ፡ በሕይወቴ
ሌላው ፡ ሌላው ፡ ይሆናል ፡ አለው ፡ ጊዜው
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት
እንዳሳቡ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ
እንዲደረግ ፡ እናውቃለን (፪x) [1]
|