From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ክረምት ፡ አለፈ ፡ ጐርፎ ፡ አልፎ ፡ ሄደ
በለስ ፡ ጐመራ ፡ ወይኑም ፡ አበበ
ዘመን ፡ ተሰማ ፡ ለፍጥረት ፡ ሁሉ
ምህረቱ ፡ በዝቷል ፡ እስቲ ፡ እልል ፡ በሉ
አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን
ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x)
ከቅጥሬ ፡ ኋላ ፡ እርሱ ፡ ቆሞልኝ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልኝ
እንዲህ ፡ ያደረገ ፡ ያ ፡ መድሃኒቴ
ዘመን ፡ ማጣልን ፡ ሰምቶ ፡ ጩኸቴን(፪x)
አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን
ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x)
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ ፡ የዕልልታዬ (፬x)
መንጊያውን ፡ ስከተል ፡ ከኋላ ፡ ኋላ
ምኞቴ ፡ ሃሳቤ ፡ ነበረ ፡ ሌላ
ፍቅሩ ፡ ወደቀ ፡ ከእረኛው ፡ ላይ
ንጉሥ ፡ አደረገኝ ፡ የለበት ፡ ከልካይ
አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን
ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x)
ከቅጥሬ ፡ ኋላ ፡ እርሱ ፡ ቆሞልኝ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልኝ
እዘምራለሁ ፡ ሆኜ ፡ አለቱ ፡ ላይ
የዝማሬ ፡ ድምጽ ፡ ይግባልኝ ፡ ሰማይ(፪x)
አዝ፦ ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ዘመን
ዘመን ፡ መጣልኝ ፡ ለእኔማ
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ (፪x)
የዕልልታዬ ፡ ድምጽ ፡ ሊሰማ ፡ የዕልልታዬ (፬x)
|