የሚያስብለኝ (Yemiyasbelegn) - መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ
(Mekashaw Kassa & Tsebaot Engeda)

Lyrics.jpg


(1)

ዘመን ፡ መጣልኝ
(Zemen Metalegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Mekashaw Kassa & Tsebaot Engeda)

 
አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ ፀጋ ፡ የሚያግዘኝ
የሚራራልኝ ፡ አምላክ ፡ የሚያስብልኝ
እያለኝ (፬x)
ምነው ፡ መጨነቄ ፡ ምነው ፡ መረበሼ ፡ ምነው(፪x)
አምላክ ፡ እንደ ፡ ሌለው
ኧረ ፡ ምነው (፫x) ፡ አምላክ ፡ እንደሌለው
ኧረ ፡ ምነው (፫x) ፡ ጌታ ፡ እንደሌለው

እናት ፡ ልጇን ፡ ትረሳለች
ደግሞም ፡ ሲላት ፡ ትተዋለች
ወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ልክ ፡ አላቸው
ወንድም ፡ እህት ፡ ለፍቅራቸው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ የወደደኝ
እስከሞት ፡ ነው ፡ የታመነኝ
(፬x)
የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ የወደደኝ
እስከሞት ፡ ነው ፡ የታመነኝ

ጉልበት ፡ ??? ፡ ተስፋ ፡ ???
ሰማይ ፡ ተቁሮ ፡ ምድር ፡ ????
በሰልፍ ፡ ቀን ፡ መከታዬ ፡ የምትራራ ፡ ኧረኛዬ
አለህልኝ ፡ ዛሬም ፡ ጠበቃዬ
በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ
(፭x)

የቆምኩበት ፡ ሲንሸራተት ፡ ቀን ፡ ጨለማ ፡ ሲሆንበት
አለሁ ፡ ያሉኝ ፡ ሲበተኑ ፡ በቃላቸው ፡ ሲፈተኑ
ፀጋህ ፡ ለእኔ ፡ መልስ ፡ ሆኖኛል
ታዲያ ፡ ለምን ፡ ያሰጋኛል
(፭x)

አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ ፀጋ ፡ የሚያግዘኝ
የሚራራልኝ ፡ አምላክ ፡ የሚያስብልኝ
እያለኝ (፬x)
ምነው ፡ መጨነቄ ፡ ምነው ፡ መረበሼ ፡ ምነው(፪x)
አምላክ ፡ እንደ ፡ ሌለው
ኧረ ፡ ምነው (፫x) ፡ አምላክ ፡ እንደሌለው
ኧረ ፡ ምነው (፫x) ፡ ጌታ ፡ እንደሌለው