የጌታ ፡ መንፈስ (Yegieta Menfes) - መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ
(Mekashaw Kassa & Tsebaot Engeda)

Lyrics.jpg


(1)

ዘመን ፡ መጣልኝ
(Zemen Metalegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Mekashaw Kassa & Tsebaot Engeda)

 
የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x)
የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x)

አሃሃሃ ፡ ጠላቴ ፡ ሊያመልጥ ፡ ለምን ፡ ይሞክራል
የእግዚአብሔር ፡ እሳት ፡ ዙሪያውን ፡ ከቦታል
ኤልያስ ፡ የእስራኤል ፡ ነው ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ሆኗል
እግዚአብሔር ፡ ቅባቱን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ለቆታል

የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው(፪x)
ለታሰሩት ፡ መፈታት ፡ ላዘኑት ፡ መጽናናት ፡ እናገር ፡ ዘንድ ፡ ልኮኛል
ጌታ ፡ መንፈሱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነው

እግዚአብሔር ፡ የቀባኝ ፡ ሰልፍን ፡ ያስተማረኝ
ጐልያድን ፡ እንድመታ ፡ ያንን ፡ ያዝጋጀኝ
ልባቹህ ፡ አይውደቅ ፡ በጩኸቱ ፡ ብርታት
ተመቶ ፡ ይወድቃል ፡ በአምላኬ ፡ ጉልበት

የጨለማ ፡ ስልጣን ፡ ጥቃት ፡ በዝቶበታል
የእኔ ፡ ነው ፡ ያለውን ፡ ለቆ ፡ ሲሸሽ ፡ ታይቷል
ፓውሎስ ፡ ጴጥሮስ ፡ የሉም ፡ እኛን ፡ ተክተዋል
ለእኔ ፡ ለአንተ ፡ ለአንቺ ፡ አደራ ፡ ሰጥተዋል

የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x)
የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ፡ ይለኛል ፡ ሰይፉን ፡ አሲዞ(፫x)