From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የፈሰሰ ፡ ውኃ ፡ በቃ ፡ አይታፈስም
ዳግመኛ ፡ ሊጠቅም ፡ እድልም ፡ የለውም
ሰው ፡ ተስፋ ፡ ሲቆርጥ ፡ እንዲህ ፡ ይተርታል
የሞተው ፡ ሊቀብር ፡ አልቅሶ ፡ ይወጣል
ጌታ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የፈሰሰም ፡ ውኃ ዳግም ፡ ይታፈሳል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሞቷል ፡ የተባለ ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል
ጌታ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ አይቻልም ፡ ሚባል ፡ ቃል ፡ ከቶ ፡ አይገኝም
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የወደቀ ፡ ይነሳል ፡ ተቆርጦ ፡ አይጣልም
አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ
አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ
ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ
ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ
(ኢየሱስ) ፡ ተስፋ ፡ በጠፋበት ፣ (ኢየሱስ) ፡ ተስፋ ፡ ትሆናለህ
(ኢየሱስ) ፡ ታሪክን ፡ በታሪክ ፣ (ኢየሱስ) ፡ ትለዋውጣለህ
(ኢየሱስ) ፡ የጠበቁህ ፡ አያፍሩም ፣ (ኢየሱስ) ፡ በጽናት ፡ የቆዩ
(ኢየሱስ) ፡ በረሃው ፡ ለምልሞ ፣ (ኢየሱስ) ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ አዩ
አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ
አምላኬ ፡ ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ
ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ
ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ
ሞት ፡ ጥላውን ፡ አቅልጦ___፡ ፍርሃት ፡ ሲነግስ
እምነትን ፡ ሊናጠቅ ፡ ጠላት ፡ ሲገሰግስ
የሕይወት ፡ ምዕራፎች ፡ ትግላቸው ፡ በርትቶ
ተስፋ ፡ ያደረጉት ፡ ሳይገኝ ፡ ዘግይቶ
(ጌታ ፡ ያኔማ) ፡ ድንገት ፡ ዘምበል ፡ ስትል ፡ ሁሉም ፡ ይለወጣል
(ኢየሱስ ፡ ያኔማ) ፡ የተመሳቀለው ፡ በቃልህ ፡ ይሰናዳል
(ጌታ ፡ ያኔማ) ፡ ዘመን ፡ ስታመጣ ፡ እስከመቼ ፡ ላሉ
(ኢየሱስ ፡ ያኔማ) ፡ በምሥጋና ፡ ሆነው ፡ ታስበናል ፡ ላሉ
ትችላለህ ፡ ታሪክን ፡ መለወጥ
ትችላለህ ፡ መራራውን ፡ ማጣፈጥ (፪x)
|