From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አምላኬ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት ፡ ለአንተ ፡ እሰዋለሁ
አምላኬ ፡ ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ትቼ ፡ እኔ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
አይጓደልብህ ፡ ምሥጋናዬ ፣ አይጓደልብህ ፡ አምልኮዬ(፪x)
በሰልፉ ፡ መሃል ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
ሃዘን ፡ ለቅሶዬን ፡ ትቼ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
እዘምራለሁ (፬x)
በጭካኔ ፡ በትር ፡ በብዙ ፡ ቆሳስለው
ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ እስር ፡ ቤት ፡ ተጥለው
ጸጥታው ፡ ይሰፍናል ፡ ወትሩም ፡ ሲሆን ፡ ሌሊት
ያኔ ፡ ግን ፡ ይሰማል ፡ ቁስለኛው ፡ ሲያቃስት
ይጠበቅ ፡ ነበር ፡ ማቃሰታቸው
ግን ፡ ተቀየረ ፡ ሌሊት ፡ ድምጻቸው
ሁኔታን ፡ ትተው ፡ ሲያመሰግኑ
የጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ታየ ፡ ማዳኑ
ዘምር ፡ ዘምር ፡ ይለኛል ፡ ኢየሱስን ፡ ሳስበው
አመስግነው ፡ ይለኛል ፡ ኢየሱስን ፡ ሳስበው (፪x)
ምሥጋናዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና
አምልኮዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና
ዝማሬዬ ፡ ይጨምራል ፡ ገና (፪x)
ንጉሥ ፡ እዮሳፍጥ ፡ ጠላቶች ፡ ከበውት
ንግስናውን ፡ ሊሽሩ ፡ እርስቱን ፡ ሊነጥቁት
የአባቶቹ ፡ አምላክ ፡ ፊቱን ፡ ቢፈልገዉ
ሰልፍ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ልቡን ፡ አሳረፈዉ
ምሥጋናን ፡ ይዞ ፡ ወጣ ፡ አደባባይ
ድልን ፡ አገኘ ፡ በጠላቱ ፡ ላይ
የአምላክ ፡ ድብቅ ፡ ጦር ፡ ተንቀሳቀሰ
ጠላት ፡ እርስ ፡ በእርስ ፡ ተጨራረሰ
አላወራውም ፡ የጠላቴን ፡ ሰልፍ ፡ ሃይለኛ ፡ ብዬ
አላወራውም ፡ አላስተጋባም ፡ ምሥጋናን ፡ ጥዬ
(ልማዴ ፡ ነው) ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ለአንተ ፡ መጨመር
(ልማዴ ፡ ነው) ፡ ሁኔታን ፡ ትቶ ፡ ለአንተ ፡ መዘመር
(ባህሌ ፡ ነው) ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ መጨመር
(ባህሌ ፡ ነው) ፡ ሁኔታን ፡ ትቶ ፡ ለአንተ ፡ መዘመር
ልማዴ ፡ ነው (፪x)
ባህሌ ፡ ነው (፪x)
|