ሃሌሉያ (Hallelujah) - መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ
(Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

Lyrics.jpg


(1)

ዘመን ፡ መጣልኝ
(Zemen Metalegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

(እብራይስጥ ፡ ቋንቋ)

አዝ፦ ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)
ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)

እረኛ ፡ እንደሌለው ፡ በጐች ፡ ተቅበዝብዘን
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ከላይ ፡ አይቶ ፡ አዘነልን
የሞትን ፡ ቀኝ ፡ ሰብሮ ፡ በድል ፡ ላራመደን
በአደባባይ ፡ ቆመን ፡ ክብር ፡ እንላለን (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፬x)
ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)

የጽዮንን ፡ ምርኮ ፡ በመለሰ ፡ ጊዜ
እንባችን ፡ ታብሶ ፡ ወታን ፡ ከትካዜ
በዙሪያችን ፡ ያሉ ፡ አንዲህ ፡ ሲሉ ፡ ሰማን
ድንቅ ፡ ነው ፡ አምላካቸው ፡ እኛም ፡ አይተነዋል (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፬x)
ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)

በእግዚአብሔር ፡ በትር ፡ አለቱ ፡ ተመቶ
ከሚፈሰው ፡ ጅረት ፡ ሕይወታቸው ፡ ረክቶ
በእንግድነት ፡ ምድር ፡ ዝማሬ ፡ ሆኖልን
ዛሬም ፡ እንዘምራለን ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ እያልን (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፬x)
ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)

አሞካሸን ፡ ብለን ፡ እኛም ፡ ባርከነዋል
ውዳችን ፡ ውድ ፡ ነው ፡ ማንስ ፡ ይመስለዋል
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ ይሆናቸው
ክበር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ይሁን ፡ ዝማሬያቸው (፪x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (፬x)
ባሮ ፡ ሃሽም ፡ አዶናይ (፬x)
ሃሌሉያ (፬x)

(እብራይስጥ ፡ ቋንቋ)