ባለ ፡ ግርማ (Bale Germa) - መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ
(Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

Lyrics.jpg


(1)

ዘመን ፡ መጣልኝ
(Zemen Metalegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

 
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ እኩያ ፡ የሌለው (፪x)

አዝባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ ፣ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ (፬x)
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ይተቀመጠው
የአባቶቼ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነዉ (፪x)

እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነው
እኩያ ፡ የለው ፡ አምሳያ ፡ የለው

ብዙዎች ፡ ነበሩ ፡ አንቱ ፡ የተባሉ
በአስቀመጡት ፡ ታሪክ ፡ ዛሬ ፡ ይወሳሉ
ትዝታቸው ፡ ቀረ ፡ ነበሩ ፡ ተብለው
የትላንት ፡ ደማቆች ፡ ዛሬ ፡ ታሪክ ፡ ሆነው

(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ዝናው ፡ አይቀዘቅዝ
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ስራው ፡ የማይነቅዝ
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ በክብር ፡ ይኖራል
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ ሁሉንም ፡ ይገዛል
ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ
ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ

ሃያል ፡ ነዉ ፡ ከሃያላን ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ
ብርቱ ፡ ነው ፡ ከብርቱዎች ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ

አዝባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ ፣ ባለ ፡ ግርማ ፡ ነዉ (፬x)
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ይተቀመጠው
የአባቶቼ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ነዉ (፪x)

ጽኑሃን ፡ ሃያላን ፡ የምድር ፡ ነገሥታት
መንግሥታቸው ፡ ሲወድቅ ፡ ባላሰቡት ፡ ሰዓት
ግብራቸው ፡ ሲዋረድ ፡ ሲሻር ፡ ሹመታቸው
ትዝታን ፡ ታቅፈው ፡ ሁሉም ፡ ሲከዳቸው

(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ መንግሥቱ ፡ ዘለዓለም
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የሚተካው ፡ የለም
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የሚመስለው ፡ ማነው
(የእኔ ፡ ጌታማ) ፡ የክብር ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ
ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነዉ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ (፪x) ፡ ነዉ

ሃያል ፡ ነዉ ፡ ከሃያላን ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ
ብርቱ ፡ ነው ፡ ከብርቱዎች ፡ በላይ ፡ አምላኬ ፡ የበላይ
ሃያል ፡ ነዉ ፡ ሃያል
ሃያል ፡ ነዉ ፡ ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነዉ (፪x)