አንተን ፡ አንተን (Anten Anten) - መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ
(Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

Lyrics.jpg


(1)

ዘመን ፡ መጣልኝ
(Zemen Metalegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመካሻው ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ፀባዖት ፡ ዕንግዳ ፡ አልበሞች
(Albums by Mekashaw Kassa and Tsebaot Engeda)

 
አዝአንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)
ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ
ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ
የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)

ሰው ፡ በልቶ ፡ ጠጥቶ ፡ ለብሶ ፡ ተሽሞንሙኖ
በየአደባባዩ ፡ ሚዛን ፡ ደፍቶ ፡ ቀኑ
ነፍሱ ፡ ግን ፡ ተራቁታ ፡ ከስታና ፡ መንምና
ነገሮች ፡ ቢሟሉም ፡ እርካታ ፡ ቢስ ፡ ሆና

ለእኔ ፡ ግን ፡ የውጪው ፡ አይደለም
ለእኔ ፡ ግን ፡ ቀዳሚው ፡ ናፍቆቴ
ለእኔ ፡ ግን ፡ የፊትህ ፡ ብርሃን
ለእኔ ፡ ግን ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ድምቀቴ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ቁስ ፡ አይተካልኝም
ለእኔ ፡ ግን ፡ አይሆነኝ ፡ እርካታ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ አብርሆትህ
ለእኔ ፡ ግን ፡ የዘመኔ ፡ ደስታ

አዝአንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)
ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ
ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ
የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)

አልናፍቀውም ፡ የዚን ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ ዝና
አልናፍቀውም ፡ ጠፊ ፡ ነው ፡ አውቃለሁ ፡ ጌታ
አልናፍቀውም ፡ አንተን ፡ ትቶ ፡ መኖር ፡ ለአፍታ
አልናፍቀውም ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ

ኢየሱስ ፡ በየትኛውም ፡ ስፍራ
ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ቁም ፡ ነገር
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ መኖር

ፊትህ ፡ ይብራልኝ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
ከምንም ፡ በላይ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ለእኔ
በሌለህበት ፡ አይሁን ፡ ኑሮዬ
መገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ መሰማሪያዬ

ነፍስን ፡ ሊያስደስቷት ፡ ቢበሉ ፡ ቢጠጡ
በሹመኞች ፡ ወንበር ፡ ደግሞም ፡ ቢቀመጡ
የሰው ፡ ልጅ ፡ ፍላጐት ፡ መች ፡ በዚህ ፡ ይረካል
የያዘውን ፡ ጠግቦት ፡ ኋላ ፡ ሌላ ፡ ያምረዋል

ለእኔ ፡ ግን ፡ የዚች ፡ ዓለም ፡ መልኳ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ጠፊ ፡ ነው ፡ ገብቶኛል
ለእኔ ፡ ግን ፡ ውስጤም ፡ አይሳሳለት
ለእኔ ፡ ግን ፡ ፍቅርህ ፡ በልጦብኛል
ለእኔ ፡ ግን ፡ መኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
ለእኔ ፡ ግን ፡ ከምንም ፡ ይበልጣል
ለእኔ ፡ ግን ፡ የማያልፍ ፡ ምርጫ
ለእኔ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ውለህልኛል

አዝአንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)
ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ ረሃቤ
ክብርህን ፡ ሳየው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
ከሁሉ ፡ የምትበልጥ ፡ ምርጫዬ
የነፍሴ ፡ እርካታ ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ፡ ልቤ (፬x)