From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ክበርልኝ...ክበርልኝ
ደሙ ፡ ደሙ ፡ ደሙ
የጌታዬ ፡ ደም ፡ ነው ፡ ደሙ
ደሙ ፡ ደሙ ፡ ደሙ
የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ነው ፡ ደሙ
ከኃጢአት ፡ ከበደሌ ፡ የነጻሁበት
እስራቴም ፡ ደግሞ ፡ የተበጠሰበት
በጐልጐታ ፡ ፈሶ ፡ ነጻ ፡ የወጣሁበት
ደሙ ፡ ደሙ ፡ ደሙ
የጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ደሙ
ደሙ ፡ ደሙ ፡ ደሙ
የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ነው ፡ ደሙ
አዝ፦ ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ፡ ምህረትህን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
አዝኜ ፡ ተክዤ ፡ በፍርሃት ፡ እያለሁ
በመስቀልህ ፡ ጉልበት ፡ ድፍረትን ፡ አገኘሁ
የፈሰሰው ፡ ደምህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው
ከብዙ ፡ እስራት ፡ ነጻ ፡ ሚያወጣ ፡ ነው
ነጻ ፡ ሚያወጣ ፡ ነው
አዝ፦ ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ፡ ምህረትህን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
የቀረኝ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ
የማትፈልገውን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳላይ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳልኝ ፡ ከሕይወቴ ፡ ላይ
አንተው ፡ ግባበት ፡ በሩጫዬ ፡ ላይ
በሩጫዬ ፡ ላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ልኖርልህ ፡ እፈልጋለሁ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ላመልክህ ፡ እፈልጋለሁ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ንገረኝ ፡ ንገረኝ ፡ ምንድንነው
ኢየሱስ ፡ ጥሩ ፡ እየኖርኩልህ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ስታየኝ
ኢየሱስ ፡ አካሄዴ ፡ እንዴት ፡ ነው ፡ እስቲ ፡ ንገረኝ (፪x)
አዝ፦ ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
ኦ ፡ የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
የዓይኖቼ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ፡ ምህረትህን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
|