ጥንትም ፡ የረዳኝ (Tentem Yeredagn) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

ጥንት ፡ ለረዳኸኝ
አሁንም ፡ እንደምትረዳኝ
ሁሌም ፡ እንደምትረዳኝ ፡ አውቃለሁ
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ አመሰግንሃለሁ
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ታምኜብህ ፡ በአንተ ፡ ሩጫዬን ፡ እቀጥላለው
የሚያቅተኝ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ እንዳልከኝ ፡ እሆናለው
ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ይዣለሁ (፪x)

ከዓለም ፡ ዕዳ ፡ ልውጣ ፡ በዚያው ፡ ቀን ፡ የምትጠብቀኝ
እንደተናገርክ ፡ ጌታ ፡ እንዲሁ ፡ አደረክልኝ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ሰላምህ ፡ ገዛኝ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ተቆጣጠረኝ
(፪x)

ጥንት ፡ ለረዳኸኝ
አሁንም ፡ እንደምትረዳኝ
ሁሌም ፡ እንደምትረዳኝ ፡ አውቃለሁ
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

እንዴት ፡ እወጣዋለው ፡ እንዴትስ ፡ አልፈዋለሁ
ብዬ ፡ ባልኩት ፡ ነገር ፡ ውስጥ ፡ የአንተን ፡ ትልቅነት ፡ አየሁ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ሰላምህ ፡ ገዛኝ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ተቆጣጠረኝ
(፪x)

ጥንት ፡ ለረዳኸኝ
አሁንም ፡ እንደምትረዳኝ
ሁሌም ፡ እንደምትረዳኝ ፡ አውቃለሁ
ስለዚህ ፡ ስለዚህ ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ተራራና ፡ ዝቅታ ፡ በሕይወቴ ፡ ሲያልፉብኝ
እንዴት ፡ እንደወጣሁት ፡ ፈጽሞ ፡ አልታወቀኝ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ሰላምህ ፡ ገዛኝ
እውነትህ ፡ ነው ፡ አዕምሮዬን ፡ ተቆጣጠረኝ
(፪x)

ማዕበልና ፡ ወጀቡ ፡ ሲያናውጡብኝ ፡ መርከቡን
ጌታ ፡ ተነሳ ፡ ገሰጸው ፡ አፈረሰበት ፡ ሃሳቡን
ወግድ ፡ ቁም ፡ አለው ፡ ቆመ ፡ ነገሩ
ጌታን ፡ ስለያዘው ፡ አያሰጥመውም ፡ አለው (፪x)

በላይ ፡ ክብር ፡ በታች ፡ ክብር
ጸንተህ ፡ ለምትኖር ፡ ለእግዚአብሔር
ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር (፬x)

የዜማ ፡ ዕቃ ፡ ይምጣ ፡ ሁሉም ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
አናግሩት ፡ መሰንቆውን ፡ ደርድሩት ፡ በገናውን
ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር (፲፪x)