ስሙኝ ፡ እንጂ (Semugn Enji) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

ስለ ፡ አንተ ፡ በጆሮዬ ፡ ከሰማሁት ፡ ይልቅ (፪x)
በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ለእኔ ፡ ሆነብኝ ፡ ድንቅ (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ ለምን ፡ እንዲህ ፡ አረክ ፡ አይባልም (፪x)
የሚሰራውን ፡ ያውቃል ፡ ፍፁም ፡ አይዘነጋም (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

ምሥጋናዬ (፬x)
ይድረስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታዬ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ህዝቡን ፡ መታደግን ፡ ያውቃል (፪x)
ካስፈለገ ፡ ደግሞ ፡ ፀሐይን ፡ ያቆማል (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ጌታ ፡ ነው
ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ የእርሱ ፡ ነው (፪x)

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ አምላክን ፡ አትጠራጠሩት
ያደርጋል ፡ ብላችሁ ፡ በእውነት ፡ እመኑት
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ አምላክን ፡ አትጠራጠሩት
ያደርጋል ፡ ብላችሁ ፡ በእውነት ፡ እመኑት
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)
እስቲ ፡ ላስታውሳችሁ ፡ ትውስ ፡ አለኝ ፡ እኔም
አምላኬ ፡ የሰራው ፡ ከዚህ ፡ ቀደም
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)
የኤርትራን ፡ ባሕር ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ከፈለው
ውኃውን ፡ እንደ ፡ ግድግዳ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አቆመው
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)
የመንፈስ ፡ የመንፈስ ፡ የመንፈሱን ፡ እንጂ
የሥጋውን ፡ መስማት ፡ ያስጥላል ፡ ከደጅ
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ይህን ፡ ያደርጋል
ከቶ ፡ ለምን ፡ አልከው ፡ አይቻለውም ፡ ወይ
ስሙኝ ፡ እንጂ (፪x)

ምሥጋናዬ (፬x)
ይድረስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታዬ (፪x)

አቤት ፡ ውበቱ ፡ የተዓምራቱ
ለጠበቀው ፡ ሰው ፡ እስከ ፡ ሰዓቱ
ሊመጣ ፡ ሲልም ፡ አረፋፈዱ
ሊነጋ ፡ ሲልም ፡ መጨላለሙ

አርፍዶ ፡ ይነሳል ፡ ሁሉን ፡ ይቀድማል
የተዓምራቱን ፡ ውበት ፡ ያሳያል (፪x)

አቤት ፡ ውበቱ ፡ የተዓምራቱ
ለጠበቀው ፡ ሰው ፡ እስከ ፡ ሰዓቱ
ሊመጣ ፡ ሲልም ፡ አረፋፈዱ
ሊነጋ ፡ ሲልም ፡ መጨላለሙ

አርፍዶ ፡ ይነሳል ፡ ሁሉን ፡ ይቀድማል
የተዓምራቱን ፡ ውበት ፡ ያሳያል (፪x)