ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (Leyet Yale New) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

አላሳልፈኝ ፡ ያለው ፡ የብረት ፡ መዝጊያው
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተከፈተ ፡ አሁን ፡ በጊዜው (፪x)

ባለስልጣኑን ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ ሲያየው
ለመከፈት ፡ መነካት ፡ አላስፈለገው (፪x)

አልፈራም ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ
እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ ተደላድዬ
አልሰጋም ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ
እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ ተደላድዬ

ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x)
ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አያለ
ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ

እሄዳለሁኝ ፡ ገና ፡ አላቋርጥም
በእኔ ፡ ያለው ፡ እርሱ ፡ ፍፁም ፡ አይደክምም (፪x)

በኃይልና ፡ በብርታት ፡ በእኔ ፡ ሳይሆን
በመንፈሱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ችላለሁ ፡ ሁሉን (፪x)

በእርሱ ፡ ታምኜ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ በክብር ፡ አድራለሁ (፪x)

ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x)
ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አያለ
ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ

እስቲ ፡ ልናገር ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ አሃ
የጠላቴን ፡ ትጥቅ ፡ አቤት ፡ ሲያስፈታ (፫x)
አደራረጉ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆ
የእኔ ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው ፤ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x)

ቀን ፡ በቀን ፡ እኔ ፡ ማየው ፡ ቀን ፡ በቀን
የሚያሳየኝ ፡ ጉድ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀን ፡ በቀን
ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ በልጧል
የማዳን ፡ እጁ ፡ ለእኔ ፡ ቀርቧል (፪x)
ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ በልጧል
የማዳን ፡ እጁ ፡ ለእኔ ፡ ቀርቧል (፪x)

በተዐምር ፡ እወጣለሁ ፡ በተዐምር ፡ እገባለሁ
የታመንኩበት ፡ ጌታዬ ፡ ተዐምረኛ ፡ ነው (፪x)

አሁን ፡ አሁንማ ፡ ብሷል ፡ አሁን ፡ አሁን (፪x)
እኔም ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱም ፡ ይሰራል
ከተዐምራቱ ፡ እኔን ፡ ያጠግበኛል (፪x)
እኔም ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱም ፡ ይሰራል
ከተዐምራቱ ፡ እኔን ፡ ያጠግበኛል (፪x)

እስቲ ፡ ልናገር ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ አሃ
የጠላቴን ፡ ትጥቅ ፡ አቤት ፡ ሲያስፈታ (፫x)
አደራረጉ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆ
የእኔ ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x)