Meheret Etefa/Leyet Yale New/Helm Alegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዮሐንስ 12፡3-

ዘማሪ ምህረት ኢተፋ ርዕስ ሕልም አለኝ

ምሥጋናም ይብዛ ይብዛ

አምልኮም ይብዛ ይብዛ

ክብርም ይብዛ ይብዛ

ውዳሴም ይብዛ ይብዛ


ይሂድ ወደ ላይ ወደ ላይ

አንተ ወዳለበት እላይ

የክብር ጌታ አምላክ ሆይ

ከፍ በል በምድር በሠማይ (፪x)


ፊትህ ይሰበር ይውደቅ ያልባስጥሮስ ሽቶ ጠርሙስ

ክብሬን ልጣለው እንጂ ሥምህን ላክብረው ልወድስ

ክብሬን ልጣለው እንጂ ሥምህን ላክብረው ልወድስ (፪x)

አንተ ስትከብር ስትነግስ ማየት

ሰውም በማዳንህ በሥራህ ሲደሰት

ከዚህም የሚበልጥ ምን አለኝ ደስታ

እስቲ የቱ ምን አለኝ ደስታ

ክብሬ ማዕረጌም ስትከብር የእኔ ጌታ


ምሥጋናም ይብዛ ይብዛ

አምልኮም ይብዛ ይብዛ

ክብርም ይብዛ ይብዛ

ውዳሴም ይብዛ ይብዛ


ይሂድ ወደ ላይ ወደ ላይ

አንተ ወዳለህበት እላይ

የክብር ጌታ አምላክ ሆይ

ከፍ በል በምድር በሠማይ (፪x)


ሕልም አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)

ተስፋ አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)

ምልስ አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)


የማምነው እርሱ ጌታዬ

ተስፋ የማደርገው ጌታዬ

አይታማም በምንም

እርሱን ጠርቶት ያፈረ የለም

እርሱን ጠርቶት ያፈረ የለም (፪x)


የአብርሃም ተስፋው ቢዘገይበት

እግዚአብሔር መጣ ቤቱን አደሰለት

ቀን ቀን አሸዋዉን ማታም ከዋክብትን

እያሳየ አረገው ሊያድስ ተስፋውን


ያም ሆነ ይህ ሆነ እንደው አይቀሬ ነው

ይስሃቅ መዘግየቱ ለደስታና ለሳቅ ነው (፪x)


ሕልም አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)

ተስፋ አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)

መልስ አለኝ እኔ የምጠብቀው

በቅርብ ይሆናል አየዋለሁ (፪x)


የማምነው እርሱ ጌታዬ

ተስፋ የማደርገው ጌታዬ

አይታማም በምንም

እርሱን ጠርቶት ያፈረ የለም

እርሱን ጠርቶት ያፈረ የለም (፪x)


የነሙሴ ጉዞ ወደ ከነዓን

ግባቸው ሕልማቸው እርሷን መውረስን

ኧረ አንተ ዮርዳኖስ ከፊት ያለው ለምን ነው

ተዓምር ሊሰራብህ ጌታም ሊከብርብህ ነው (፪x)


ምሥጋናም ይብዛ ይብዛ

አምልኮም ይብዛ ይብዛ

ክብርም ይብዛ ይብዛ

ውዳሴም ይብዛ ይብዛ


ይሂድ ወደ ላይ ወደ ላይ

አንተ ወዳለበት እላይ

የክብር ጌታ አምላክ ሆይ

ከፍ በል በምድር በሠማይ (፪x)