ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል (Feqreh Nektognal) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

ምህረትህና ፡ ቸርነትህ ፡ በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ይከተሉኛል
እለት ፡ እለት ፡ ክቡር ፡ ደሙ ፡ ይሸፍነኛል ፡ ይጠብቀኛል
ሃሌሉያ ፡ ቤትህ ፡ ያገቡኛል
ታማኙ ፡ እጅህ ፡ መቼ ፡ ይጥላል
ታማኙ ፡ እጅህ ፡ ቤት ፡ ያደርሳል (፪x)
ሃሌሉያ ፡ ቤትህ ፡ ያገቡኛል

ዝም ፡ ዝም ፡ አትበል ፡ ነፍሴ ፡ ትለኛለች
የአምላኳን ፡ ውለታ ፡ ሁሌም ፡ ታስባለች (፪x)

እንዴት ፡ የምን ፡ ዝም ፡ ዝም ፡ ዝምታ
በልቤ ፡ ለሞላው ፡ ጌታ
ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ልመስክርልህ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ ማያውቅ ፡ አለ ፡ እንዴ
ሃሌሉያ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ልውደድ

ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ በጣም ፡ እወድሃለሁ
ሁልጊዜ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ በጣም ፡ እወድሃለሁ

እንዴት ፡ የምን ፡ ዝም ፡ ዝም ፡ ዝምታ
በልቤ ፡ ለሞላው ፡ ጌታ
ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ልመስክርልህ
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ ማያውቅ ፡ አለ ፡ እንዴ
ሃሌሉያ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ልውደድ

ያለፈው ፡ ዘመኔ ፡ አለፈ ፡ አለፈ
ዳግመኛ ፡ ላላየው
ያለፈው ፡ ኑሮዬ ፡ አለፈ ፡ አለፈ
ዳግመኛ ፡ ላላየው

ቀሪውን ፡ ዘመኔን ፡ ባርከው ፡ ባርከው
የአንተው ፡ ለአንተው ፡ አድርገው
ያለአንተ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንልኝም
ከእንግዲህ ፡ እንካ ፡ ተቆጣጠረኝ
ከእንግዲህ ፡ እንካ ፡ እንካ ፡ ጌታ ፡ ተቆጣጠረኝ