እስቲ ፡ ላነሳሳው (Esti Lanesasaw) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

የእርሱን ፡ ጥበብ ፡ ታላቅነት
ምስክር ፡ ነው ፡ የሰራው ፡ ፍጥረት (፪x)
ሁሉም ፡ ያውራ ፡ ይተርክለት
ቃሉን ፡ ሥራውን ፡ ይጨዋወቱት (፪x)

እኔስ ፡ ላውራለት
ቅኔን ፡ ልቀኝለት
ቅኔን ፡ ልቀኝለት (፪x)

እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው
የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው
ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው
አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

የምድር ፡ ዕፅዋት ፡ የምድር ፡ እንስሳት
ለቅጽበት ፡ አይቆሙም ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ምህረት (፪x)
የአቀማመጥቸው ፡ አቤት ፡ የውበታቸው
ቢታቱ ፡ ቢታዩ ፡ የማይጠገቡ ፡ ናቸው (፪x)

አምልኮው ፡ ለአንተ
ዝማሬው ፡ ለአንተ
ዕልልታው ፡ ለአንተ
ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x)

እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው
የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው
ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው
አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

ሁሉን ፡ የሚችለው ፡ የአምላክ ፡ እስትንፋስ ፡ ፈጠረኝ
አበጃጀኝና ፡ ሕይወትንም ፡ ሰጠኝ (፪x)
የፈጠርከኝ ፡ ጌታ ፡ እኔም ፡ አከብርሃለው
ስለ ፡ አንተ ፡ ላወራ ፡ ይኸው ፡ መጥቻለሁ (፪x)

አምልኮው ፡ ለአንተ
ዝማሬው ፡ ለአንተ
ዕልልታው ፡ ለአንተ
ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x)

እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው
የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው
ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው
አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

አምልኮው ፡ ለአንተ
ዝማሬው ፡ ለአንተ
ዕልልታው ፡ ለአንተ
ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x)