Meheret Etefa/Leyet Yale New/Enie Ersun Yemawqew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ=ምህረት ፡ ኢተፋ
ርዕስ እኔ እርሱን የማውቀው
አልበም ለየት ያለ ነው

እንደ አፉ እንደተናገረው
ያደርጋል ጌታዬ ታማኝ ነው
እንደ አፉ እንደተናገረው
ጌታዬ ታማኝ ነው (፪x)

አዝ
እኔ እርሱን የማውቀው በመልካምነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በኃያልነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በፈዋሽነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በመሃሪነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በእውነተኛነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በታማኝነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በሰፌው ትዕግስቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በረዳትነቱ

ሰዎች ከውጭ ሆነው እንዲህ አሉኝ
እስቲ አምላኳ ያርግ አሉ ዛቱብኝ (፪x)
አምላኬም ከሠማይ ይህንን አየ
በሚያሳይበት ሰርቶ አሳየ (፪x)
ጌታዬም ከሠማይ ይህን አየ
በሚያሳይበት ሰርቶ አሳየ (፪x)

አዝ
እኔ እርሱን የማውቀው በመልካምነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በኃያልነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በፈዋሽነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በመሃሪነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በእውነተኛነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በታማኝነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በሰፌው ትዕግስቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በረዳትነቱ

እኔ እርሱን የማውቀው እንደዚህ ነው
እስራቴን ፈትቶ ሲለቀኝ ነው (፪x)

ጠላቴ ይሄን ስማ እነግርሃለው
እንደ አንተ አይደለም ጌታ ታማኝ ነው
እርሱ ታማኝ ነው (፪x)

አዝ
እኔ እርሱን የማውቀው በመልካምነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በኃያልነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በፈዋሽነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በመሃሪነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በእውነተኛነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በታማኝነቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በሰፌው ትዕግስቱ
እኔ እርሱን የማውቀው በረዳትነቱ