From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ክብሬ (፯x)
ሞገሴ
ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ
የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x)
ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ
ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ
የሞት ፡ መልአክት ፡ አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ ፡ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ፡ እኮ ፡ በደሙ ፡ ታጥሯል
ያን ፡ ቅጥር ፡ አልፎ ፡ እንዴት ፡ ይገባል (፪x)
ለጠላቴ ፡ የሃዘን ፡ ለእኔ ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው
ሞት ፡ እየገባ ፡ ያለው ፡ በጠላቴ ፡ መንደር ፡ ነው
ይዙር ፡ እንጂ ፡ ዙሪያዬን ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ
ፍፁም ፡ መቅረብ ፡ አይችልም ፡ ከደሙ ፡ የተነሳ (፪x)
ደሙ ፡ በመቃኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ደሙ ፡ በጉበኔ ፡ ላይ ፡ ስለተቀባ
ሞት ፡ አለፈ ፡ ሄደ ፡ እራቀ ፡ ከእኔ ፡ ጋር
የጌታዬን ፡ ደም ፡ አይቶ
የኢየሱሴን ፡ ደም ፡ አይቶ (፪x)
ሞት ፡ አለፈ ፣ ሞት ፡ አለፈ
ሄደ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ
በአንተ ፡ ነው ፡ መኖሬ
ክብሬ (፯x)
ሞገሴ
|