From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በዋጋ ፡ ገዛኸኝ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት (፪x)
በዋጋ ፡ ገዛኸኝ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት (፪x)
ሃዘን ፡ መከራዬን ፡ ረሳሁ
በፊቱ ፡ ሞገስ ፡ አገኘሁ (፪x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር
ለዚህ ፡ መብቃቴ ፡ እንዲህ ፡ መሆኔ
በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ነው ፡ መች ፡ በእኔ
ክብር ፡ ይድረሰው ፡ መድህኔ
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር (፯x)
አይደለም ፡ በእኔ ፡ በእኔ ፡ በኃይሌ
አይደለም ፡ በእኔ ፡ በእኔ (፪x)
ቅንነትህ (፫x)
አሰረኝ ፡ አሰረኝ ፡ የዋህነትህ
አንተ ፡ ቅንና ፡ ቸር ፡ የዋህ
ትህትናን ፡ ለሁሉ ፡ አስተማርክ
ከሃጥያት ፡ በቀር ፡ ስለሰው
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ተፈተንክ ፡ አሃ
ተፈተንክ
ቅንነትህ (፫x)
አሰረኝ ፡ አሰረኝ ፡ የዋህነትህ
የግሌ ፡ ነህ ፡ የእራሴ
የብቻዬ ፡ ጌታዬ ፡ ለእኔ (፪x)
አይደለም ፡ በእኔ ፡ በእኔ ፡ በኃይሌ
አይደለም ፡ በእኔ ፡ በእኔ
አይደለም ፡ በእኔ
ቅንነትህ (፫x)
አሰረኝ ፡ አሰረኝ ፡ የዋህነትህ
ክብሩ (፫x)
ለእግዚአብሔር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁንለት
ስራዬን ፡ ሰራልኝ ፡ አገኘሁ ፡ ነጻነት
ድንቅ ፡ ነው (፫x)
ሥራው ፡ አቤት ፡ ሲችልበት
ጠላትን ፡ ማንበርከክ ፡ አቤት ፡ ሲችልበት
እግዚአብሔር ፡ ቀደመ ፡ ኦሆሆሆ
ጠላቴን ፡ ገጠመ ፡ ኡሁሁ
ደገመ ፡ ደገመ ፡ ኦሆሆሆ
ፊቴ ፡ እየቀደመ ፡ ኡሁሁ (፪x)
ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ለማን ፡ ይበገራል
እግዚአብሔርን ፡ አይቶ ፡ ጠላቴም ፡ ፈርቶኛል (፪x)
ይሄ ፡ ነው (፭x)
ጌታ ፡ ድል ፡ አድራጊው (፪x)
|