በሥራው (Beseraw) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

በሥራው ፡ ትክክል ፡ በሥራው ፡ የማይሳሳት
በሥራው ፡ አንድ ፡ እንኳን
ሥራው ፡ ሥራው ፡ እንከን ፡ የሌለው (፪x)

የማይሆነውን ፡ ነገር ፡ አይሆንም ፡ እያለ
የማይረባኝንም ፡ እየከለከለ
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ እኔን ፡ እያባበለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ እሹሩሩ ፡ እያለ
እሹሩሩሩሩ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ
ነይ ፡ ልጄ (፫x) ፡ እያለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ

እኔንም ፡ መራኝ ፡ እንጂ ፡ እጄን ፡ በእጁ ፡ ይዞ
እያሸጋግረኝ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ጉዞ
ማዕበልና ፡ ወጀቡን ፡ በሥልጣኑ ፡ አዞ
የሚነሳብኝን ፡ ጠላቴን ፡ ገስጾ

እቅፍ ፡ እቅፍ ፡ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ አርጐ
መራኝ ፡ እርሱ ፡ መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ (፬x)

የማይሆነውን ፡ ነገር ፡ አይሆንም ፡ እያለ
የማይረባኝንም ፡ እየከለከለ
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ እኔን ፡ እያባበለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ እሹሩሩ ፡ እያለ
እሹሩሩሩሩ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ
ነይ ፡ ልጄ (፫x) ፡ እያለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ

ህጻን ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ እንደ ፡ ህጻንነቴ
መራኝ ፡ ተንከባክቦ ፡ እንደ ፡ እናት ፡ እንደ ፡ አባቴ
አሁንም ፡ ባለሁበት ፡ እንደ ፡ እኔነቴ
ያኖረኛል ፡ በድል ፡ . (1) . ፡ ከፊቴ

እቅፍ ፡ እቅፍ ፡ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ አርጐ
መራኝ ፡ እርሱ ፡ መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ (፬x)

በሥራው ፡ ትክክል ፡ በሥራው ፡ የማይሳሳት
በሥራው ፡ አንድ ፡ እንኳን
ሥራው ፡ ሥራው ፡ እንከን ፡ የሌለው (፪x)

የማይሆነውን ፡ ነገር ፡ አይሆንም ፡ እያለ
የማይረባኝንም ፡ እየከለከለ
በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ እኔን ፡ እያባበለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ እሹሩሩ ፡ እያለ
እሹሩሩ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ
ነይ ፡ ልጄ (፫x) ፡ እያለ
መራኝ ፡ እጄን ፡ ይዞ ፡ ነይ ፡ ልጄ ፡ እያለ