From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የማይታየውንና ፡ የሚታየውን ፡ በሙሉ
በአንተ ፡ ተፈጠረ ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ በሙሉ
በአንተ ፡ ተፈጠረ ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ በሙሉ
ትርጉም ፡ አለው ፡ ሁሉም ፡ አስተውሎ ፡ ተመለከተው
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነ ፡ ያልሆነውስ ፡ አንዳች ፡ የቱ ፡ ነው (፪x)
ተወሰደ ፡ ልቤ ፡ በእሱኛው ፡ በእሱኛው
ሰው ፡ በሰራው ፡ ሳይሆን ፡ እግዚአብሔር ፡ በሰራው
ተማረከ ፡ ልቤ ፡ በእሱኛው ፡ በእሱኛው
በምድራዊው ፡ ሳይሆን ፡ በሠማያዊው ፡ ነው
አይ ፡ ጥበብ ፡ ሆሆ
አይ ፡ ጥበብ (፬x)
አይሰራ ፡ አይ ፡ ጥበብ ፡ ረቂቅ ፡ ነው
በእርግጥ ፡ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ዕውቅታም ፡ ነው (፪x)
የኮረብታውና ፡ የወንዙ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ
ጌታ ፡ በእጁ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ በቃሉ ፡ ብቻ ፡ ፈጠረ
በእጁ ፡ ሳይነካ ፡ በቃሉ ፡ ብቻ ፡ ፈጠረ
የውቂያኖስና ፡ የባሕር ፡ የጥልቀቱ
ትልቅ ፡ ነው ፡ ያሰኛል ፡ የጌታ ፡ አቤት ፡ ዕውቀቱ (፪x)
በሥራው ፡ በዕውቀቱ ፡ የተደነቀው
ፈጣሪውን ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ
የሁሉ ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የሆነው
እኔ ፡ የማመልከው ፡ እግዚአብሔር ፡ ጌታ ፡ ነው
አይ ፡ ጥበብ ፡ ሆሆ
አይ ፡ ጥበብ (፬x)
አይሰራ ፡ አይ ፡ ጥበብ ፡ ረቂቅ ፡ ነው
በእርግጥ ፡ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ዕውቅታም ፡ ነው (፪x)
|