አጠገቤ (Ategebie) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

Meheret Etefa 4.jpg


(4)

ለየት ፡ ያለ ፡ ነው
(Leyet Yale New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

ሀ ፡ ሁ ፡ ጌታ (፪x)

አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ
እርሱ ፡ ይቀርበኛል
መገኘቱ ፡ ህልውናው ፡ ይታወቀኛል (፪x)
ከውንድም ፡ ይልቅ ፡ ይጠጋጋኛል
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል

ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x)
በልቤ ፡ ያለህ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ
ዘውትር ፡ ላክብርህ ፡ ሁሌ ፡ ጥዋት ፡ ማታ

ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው
ከሚነካኝ ፡ ከምነካው ፡ ከሚዳስሰኝ ፡ ከምዳስሰው
በዓይኑ ፡ ከሚያየኝ ፡ በዓይኔ ፡ ከማየው
እርሱ ፡ ለእኔ (፫x) ፡ ቅርቤ ፡ ነው
በገባሁበት ፡ አብሮ ፡ ይገባል
በሄድኩበት ፡ አብሮ ፡ ይሄዳል

እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ
ታዲያ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
አያያያያያያያ
እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ
ታዲያ ፡ ከየት ፡ ይገኛል (፪x)

ሥም ፡ ሰማዬ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል
እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
መኖሩን ፡ ደስ ፡ በሚለው ፡ መንፈሱ ፡ ይገልጥልኛል (፪x)
አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ
እርሱ ፡ ይቀርበኛል (፪x)

ስፍራን ፡ አይመርጥም
ጊዜን ፡ አይመርጥም (፬x)

ሀ ፡ ሁ ፡ ጌታ (፪x)

አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ ፡ እርሱ ፡ ይቀርበኛል
መገኘቱ ፡ ህልውናው ፡ ይታወቀኛል (፪x)
ከውንድም ፡ ይልቅ ፡ ይጠጋጋኛል
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል

ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x)
በልቤ ፡ ያለህ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ
ዘውትር ፡ ላክብርህ ፡ ሁሌ ፡ ጥዋት ፡ ማታ

ታማኝ ፡ ወገኔ ፡ ያለኝ ፡ በጐኔ
ታማኝ ፡ ወዳጄ ፡ ያለኝ ፡ በእጄ
በፍቅሩ ፡ ውበት ፡ ሁሉ ፡ የማትለየኝ
ታላቁ ፡ ጌታ ፡ የምትወደኝ
ታላቁ ፡ ኢየሱስ ፡ የምትመራኝ (፪x)