Meheret Etefa/Balegirma/Qenien Eqegnalehu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ፦ ምህረት ኢተፋ ርዕስ፦ ቅኔን እቀኛለሁ አልበም፦ ባለ ግርማ

አዝ፦ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ
የእጆቹን ሥራ እያየሁ
ትርጉም አለው ለእኔ
ይሄ ሁሉ የማየውን አሃሃሃ
በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ
አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (፪x)


የፈጠራቸውን ፡ ፍጥረቶች ፡ እያየሁ

ጌታን ፡ ከልብ ፡ ሆኜ ፡ አመሰግናለሁ ፦ (፪x)

አቤት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ሥራው አይቆጠር

እዘምራለሁኝ ፡ ለጌታዬ ፡ ክብር ፦ (፪x)


አዝ፦ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ
የእጆቹን ሥራ እያየሁ
ትርጉም አለው ለእኔ
ይሄ ሁሉ የማየውን አሃሃሃ
በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ
አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (፪x)


ውበትን ፡ አገኙ ፡ ሰማያት ፡ በመንፈስህ

የዓለምን ፡ ተራሮች ፡ በቃልህ ፡ አጸናህ ፦ (፪x)

እኔም ፡ ስለነሱ ፡ ክብርን ፡ እሰጥሃልሁ

የፍጥረት ፡ ፈጣሪ :ተባርክ ፡ ብያለሁ ፦(፪x)


አዝ፦ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ
የእጆቹን ሥራ እያየሁ
ትርጉም አለው ለእኔ
ይሄ ሁሉ የማየውን አሃሃሃ
በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ
አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (፪x)


የሚታየውንም ፡ ማይታየውንም

በላይ ፡ ሠማይ ፡ ቢሆን ፡ ፦በታች ፡ በምድርም ፦(፪x)

ሁሉን በየስፍራው አስተካክሎ አኖረው

አቤት አቤት ሥራው ፦እግዚአብሔር ጌታ ነው ፦(፪x)


አዝ፦ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ
የእጆቹን ሥራ እያየሁ
ትርጉም አለው ለእኔ
ይሄ ሁሉ የማየውን አሃሃሃ
በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ
አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (፪x)