Meheret Etefa/Balegirma/Balegirma

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ምህረት ፡ ኢተፋ ርዕስ ባለግርማ አልበም ባለግርማ

አዝ

ባለግርማ ባለግርማ ምሥጋና እና አምልኮዬ ማደሪያህ ይግባ (፪x) ባለሞገስ ባለሞገስ ምሥጋና እና አምልኮዬ ማደሪያህ ይድረስ (፪x)


ከአንተ በቀር አምላክ እኔ አላመልክም ሌላ ሌላውን ልቤ አልፈቀደም እሺ አላለኝም (፪x)

ባለግርማ ባለግርማ ምሥጋና እና አምልኮዬ ማደሪያህ ይግባ (፪x)

እንደ ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጐም ሰባት እጥፍ እሳቱ ቢነድም ለቆመው ምስል አልዘምርም አላደርገውም ሰባት እጥፍ ይንደድ ምን ቸገረኝ የማመልከው ይችላል ሊያድነኝ በፈቃዴ እገባለሁ ይልቀቁኝ አያቃጥለኝ

አዝ

እንደ ዳንኤል እንደ እግዚአብሔር ሰው በአንበሶች ጉድጓድ እንደ ተጣለው ግዑዙን አምላክ አላመልክም አላደርገውም

ይራቡ አንበሶቹ ምን ቸገረኝ የማመልከው ከኔጋር ካለልኝ ልሂድ ልግባ ግድ የለም ይልቀቁኝ አይችሉም ሊበሉኝ

አዝ

ለእርሱ ክብር አፌን እከፍታለሁ ደስ እያለኝ እዘምርለታለሁ ጐንበስ ቀና እያልኩኝ ለእርሱ እሰግድለታለሁ እርሱ እኮ ነው በሕይወት ያኖረኝ መከራዬን በሙሉ ያስረሳኝ አልሰለችም እወድሰዋለሁ አመልከዋለሁ

አዝ