ሳቅ ፡ አድርጐልኛል (Saq Adergolegnal) - ማሜ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ማሜ ፡ ወርቁ
(Mamay Worku)

Mamay Worku 1.jpg


(1)

ህልሜ
(Helmie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የማሜ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Mamay Worku)

አዝ፦ ሳቅ ፡ ሳቅ (፪x) ፡ ሳቅ ፡ አድርጐልኛል
ሳቅ (፫x) ፡ ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ሆኖልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ፈቃዱን ፡ ፈጽሞልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ኪዳኑን ፡ አጽንቶልኛል (፪x)

በልቤ ፡ ሞልቶ ፡ ሃዘኔን ፡ ወስዶ
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ወዲያ ፡ አባሮ
ሞላልኝ ፡ መሻቴ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ በአምላኬ
ሰጠኝ ፡ እንደልቤ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ በአምላኬ (፪x)

አዝሳቅ ፡ ሳቅ (፪x) ፡ ሳቅ ፡ አድርጐልኛል
ሳቅ (፫x) ፡ ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ሆኖልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ፈቃዱን ፡ ፈጽሞልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ኪዳኑን ፡ አጽንቶልኛል

ተጣልኩኝ ፡ ልሞት ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ጠላት
ገባሁኝ ፡ ለግዞት ፡ ያሰረኝ ፡ መስሎት
ዘመን ፡ ሲመጣ ፡ ቀኑ ፡ ሲገለጥ
የተከሰስኩበት/ተታማሁበት) ፡ ሆነልኝ ፡ ለሹመት (፪x)

አዝሳቅ ፡ ሳቅ (፪x) ፡ ሳቅ ፡ አድርጐልኛል
ሳቅ (፫x) ፡ ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ሆኖልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ፈቃዱን ፡ ፈጽሞልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ኪዳኑን ፡ አጽንቶልኛል

አይችልም ፡ አልልም ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው
አይሆንም ፡ አልልም ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ የሰው ፡ ነገር
የማይሰማ ፡ የለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር (፪x)

አዝሳቅ ፡ ሳቅ (፪x) ፡ ሳቅ ፡ አድርጐልኛል
ሳቅ (፫x) ፡ ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ሆኖልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ፈቃዱን ፡ ፈጽሞልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ኪዳኑን ፡ አጽንቶልኛል (፪x)

አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ፈቃዱን ፡ ፈጽሞልኛል
አምላኬ ፡ አስቦልኛል ፡ ኪዳኑን ፡ አጽንቶልኛል (፬x)