ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጥራው (Gieta Amlakie Beyie Seteraw) - ማሜ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ማሜ ፡ ወርቁ
(Mamay Worku)

Mamay Worku 1.jpg


(1)

ህልሜ
(Helmie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የማሜ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Mamay Worku)

አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)

ጠላቴ ፡ ሲከሰኝ ፡ አሃሃ ፡ ድካሜን ፡ ሲያሳየኝ ፡ ኦሆሆ
ኃይል ፡ ሆነልኝ ፡ ለእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ አገዘኝ (፪x)
እራሴን ፡ ቀብቶ ፡ ኦሆሆ ፡ በመቅደሱ ፡ አቆመኝ ፡ አሃሃ
እንደ ፡ መልካም ፡ እርሻ ፡ ውብ ፡ መዓዛ ፡ ሰጠኝ (፪x)

አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)

በደሌን ፡ ኀጢአቴን ፡ አሃሃ ፡ በደሙ ፡ አጠበና ፡ ኦሆሆ
ለእኔም ፡ አንደ ፡ ያዕቆብ ፡ ሥሜን ፡ ለወጠና
ታሪክ ፡ ቃየረና
የራሱ ፡ አደረገኝ ፡ ኦሆሆ ፡ በሥሙ ፡ ተጠራሁ ፡ አሃሃ
በቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ልኖር ፡ አስከብሬው ፡ እንድኖር

አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)

ዝማሬ ፡ የሰማ ፡ አሃሃ ፡ በባዕድ ፡ አገር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ
ሊያስጥለኝ ፡ ተነሳ ፡ ውዴን ፡ ከእጄ ፡ ላይ
እኔን ፡ ከእርሱ ፡ ሊለይ
እኔ ፡ ግን ፡ ተስፋዬን ፡ አሃሃ ፡ ላልረሳ ፡ ምያለሁ ፡ ኦሆሆ
ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ ፡ ተደላድያለሁ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)

የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ኦሆሆ
የተማመንኩበት ፡ ሥሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
እግሮቼን ፡ ጠብቆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኃይልን ፡ አስታጥቆኛል ፡ አሃሃ
በከፍታዎቹ ፡ በክብሩ ፡ አራምዶኛል ፡ በድል ፡ አቁሞኛል

አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ
ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው
ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)