ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (Eyesus Gieta New) - ማሜ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ማሜ ፡ ወርቁ
(Mamay Worku)

Mamay Worku 1.jpg


(1)

ህልሜ
(Helmie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የማሜ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Mamay Worku)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

ማኅተሙን ፡ የፈታ (ጌታ)
በሞት ፡ ያልተረታ (ጌታ)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ አለቃ (ጌታ) (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

ፍጥረት ፡ ሊሰግዱለት (ጌታ)
የወጉትም ፡ ሊያዩት (ጌታ)
በክብሩ ፡ ይመጣል ፡ ደምቆ ፡ ከከዋክብት (ጌታ) (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

መንግሥቱን ፡ ሊያሰፋ (ጌታ)
ዙፋኑን ፡ ሊያጸና (ጌታ)
በአጀብ ፡ ይመለሳል ፡ ከመላእክቱ ፡ ጋራ (ጌታ) (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

አሜን ፡ ማራናታ (ጌታ)
አሁን ፡ ማራናታ (ጌታ)
የንጋቱ ፡ ኮከብ ፡ የፍጥረት ፡ አለኝታ (ጌታ) (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ጊዜ ፡ የማይሽረው ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ዘመን ፡ የማይሽረው ፡ ንጉሥ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው