እኔ ፡ ግን (Enie Gen) - ማሜ ፡ ወርቁ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ማሜ ፡ ወርቁ
(Mamay Worku)

Mamay Worku 1.jpg


(1)

ህልሜ
(Helmie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2008)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የማሜ ፡ ወርቁ ፡ አልበሞች
(Albums by Mamay Worku)

የጽድቅን ፡ ጥሩር ፡ ለብሼ
ገነትም ፡ ጋሻ ፡ አንስቼ
በቃል ፡ እውነት ፡ ታጥቄ
እቆማለሁ ፡ ፀንቼ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x)

በፍጹም ፡ ልቤ ፡ እሰግዳለሁ
ሃሳቤን ፡ አስገዛለሁ
በፈቃዴ ፡ እሸነፋለሁ
ጌታዬን ፡ አመልከዋለሁ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x)

በጽኑ ፡ ምክሩ ፡ ታምኜ
በቅን ፡ ስርዓቱ ፡ ሄጄ
ቅዱስ ፡ ሥሙን ፡ አከብራለሁ
አምላኬን ፡ አመልከዋለሁ (፪x)

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x)

እግዚአብሔርን ፡ እባርካለሁ
ምሥጋናውም ፡ ሁሉ ፡ በአፌ ፡ ነው
በእርሱ ፡ ፍቅር ፡ አኖራዋለሁ
ዘለዓለም ፡ አመልከዋለሁ

አዝ፦ እኔ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመልካለሁ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፬x)