ሊዲያ ፡ አንተነህ (lidya anteneh)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ



አንተን እያመለኩ አንተን እያከበርኩ ውዴ እያመለኩ ውዴ እየወደድኩ ላንተ እየዘመርኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ አንተን እየወደድኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ በደስታ በሙሉ ልቤ ሳልሸራርፍ ይኸው ቃላቴ ባይገኝ ሚመጥንህም አመልክሀለሁ እየኖርኩ ትላንትን በሕያውነትህ ዛሬንም በዐዲስነትህ ነገንም በዘላለም ቤትህ ላምልክህ ኾኜ በፊትህ... ኑሮዬ ይኹን መሥዋዕትህ ሕይወቴም ይኸው በፊትህ በፍቅር፣ በእምነት በተስፋ አመልክሀለሁ እየኖርኩ ትላንትን በሕያውነትህ ዛሬንም በዐዲስነትህ ነገንም በዘላለም ቤትህ ላምልክህ ኾኜ በፊትህ.... አመልክሀለሁ እየኖርኩ...