አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ (Ante Gen Yaw Ante Neh) - ሊድያ ፡ (ሊሊ) ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሊድያ ፡ (ሊሊ) ፡ ተስፋዬ
(Lidiya Tesfaye)

Lidiya Tesfaye 1.jpg


(1)

የእኔ ፡ ተራ ፡ ነው
(Yenie Tera New)

ቁጥር (Track):

()


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሊድያ ፡ (ሊሊ) ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Lidiya Tesfaye)

አይገልጽህም ፡ የእኔ ፡ ቃላት
አይገልጽህም ፡ የእኔ ፡ አንደበት
ዘውትር ፡ ለአንተ ፡ ልስገድልህ ፡ (ልስገድልህ)
ልቀኝልህ ፡ ልሁን ፡ በፊትህ ፡ (ልሁን ፡ በፊትህ)
(፪x)

(አንተ) ፡ ስትሰራ ፡ የኖርክ ፡ ከጥንት ፡ ጀምሮ
(አንተ) ፡ ሥራህ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ መቼ ፡ ተቆጥሮ
(አንተ) ፡ ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
(አንተ) ፡ አትለመድም ፡ ጌታዬ ፡ በእኔ (፪x)

አትለመድም ፡ ጌታዬ ፡ በእኔ (፫x)
አትለመድም ፡ አትለመድም ፡ ልዩ ፡ ለእኔ (፪x)

በምድር ፡ ክበብ ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ተቀምጠሃል
ፍጥረት ፡ በመገረም ፡ ተሞልቶ ፡ ያይሃል
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ያለና ፡ የነበርክ
የእኔም ፡ ጉልበት ፡ ለአንተ ፡ በፊትህ ፡ ይንበርከክ
ለሥምህ ፡ ይንበርከክ

አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (አንተ)
አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ) (፪x)

ጌታ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ጌታ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ጌታ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)

አይገልጽህም ፡ የእኔ ፡ ቃላት
አይገልጽህም ፡ የእኔ ፡ አንደበት
ዘውትር ፡ ለአንተ ፡ ልስገድልህ ፡ (ልስገድልህ)
ልቀኝልህ ፡ ልሁን ፡ በፊትህ ፡ (ልሁን ፡ በፊትህ)
(፪x)

(አንተ) ፡ አንተን ፡ ያወቀ ፡ የተረዳህ
(አንተ) ፡ እንዴት ፡ ይችላል ፡ ሳያመልክህ
(አንተ) ፡ ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ጌታ
(አንተ) ፡ በምንም ፡ ነገር ፡ የማትተካ (፪x)

አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (አንተ)
አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ) (፪x)

ጌታ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)
ጌታ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ጌታ)
ኢየሱስ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ (ያው ፡ አንተው ፡ ነህ)