አታሳፍረኝም (Atasaferegnem) - ለገሰ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለገሰ ፡ ታደሰ
(Legesse Taddese)

Legesse Taddese 1.jpg


(1)

የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ
(Yehiwot Qal Aleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2015)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለገሰ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Legesse Taddese)

የኔነህ የልቤ ተስፋ የማደርግህ
የኔነህ የቅርቤ ሁሌ የምመካብህ2x
እወራረዳለሁ አታሳፍረኝም
በስምህ አምኜ ከቶ አትጥለኝም2x
      የኔነህ የልቤ ተስፋ የማደርግህ
      የኔነህ የቅርቤ ሁሌ የምመካብህ2x

ስንቱን አለፍኩት አንተን ተደግፌ
ስንቱን ተሻገርኩ አንተ ላይ አርፌ
ይገርመኛል ይደንቀኛል በህይወት መኖሬ
ይገርመኛል ይደንቀኛል ከሞትም መትረፌ

እወራረዳለሁ አታሳፍረኝም
በስምህ አምኜ ከቶ አትጥለኝም2x
 
የሩቅ አይደለህም ቅርቤ ነህ ከስትንፋስ
ስጠራህ ምትሰማ ሰምተህ የምትመልስ
አተወኝም አንተ ክንድህ ደግፎኛል
እንዳንተ ያለ አምላክ ከወዴት ይገኛል2x

የኔነህ የልቤ ተስፋ የማደርግህ
የኔነህ የቅርቤ ሁሌ የምመካብህ2x

አልተውከኝም አልጣልከኝም አለኸኝ መድህኔ
የኤልያስ አምላክ አትርቅም (አትጠፋም) ከጎኔ
አልፈራም አልሰጋም ተደላድያለው
ከእኔ ጋራ ያለው የሚያስተማምን ነው