From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የማልጠብቀው ፡ በህልሜም ፡ በውኔ
የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ እንዳሳየኝ ፡ በዓይኔ (፪x)
ኧረ ፡ ይሄማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
ዘንድሮማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
ኧረ ፡ ይሄማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
መድኃኒቴ ፡ በሕይወቴ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው
መለኮታዊ ፡ ግርማ ፡ ሞገስ
ከአምላኬ ፡ ዙፋን ፡ ከላይ ፡ ሲፈስ (፪x)
አየሁ ፡ ሕይወቴን ፡ ሲያረሰርስ (፪x)
አየሁ ፡ ኑሮዬን ፡ ሲያረሰርስ (፪x)
የናፈኳቸው ፡ የሞተስ ፡ ምንጮጭ
ተከፍተውልኝ ፡ የሰማይ ፡ ደጆች
አየሁ ፡ ሲያጠግቡኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ እጆች (፪x)
አየሁ ፡ ሲያጠግቡኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ እጆች (፪x)
የማልጠብቀው ፡ በህልሜም ፡ በውኔ
የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ እንዳሳየኝ ፡ በዓይኔ (፪x)
ኧረ ፡ ይሄማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
ዘንድሮማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
ኧረ ፡ ይሄማ ፡ ሌላ ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነው
መድኃኒቴ ፡ በሕይወቴ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው
የትንቢቱ ፡ ቃል ፡ ሥጋን ፡ ለበሰ
የተወሰደው ፡ ምርኮ ፡ ተመለሰ (፪x)
ይኸው ፡ እንደ ፡ ንሥር ፡ ኃይሌ ፡ ታደሰ (፪x)
ይኸው ፡ እንደ ፡ ንሥር ፡ ኃይሌ ፡ ታደሰ (፪x)
የልምላሜ ፡ የመጐገብኘት
የሞገስና ፡ የመፅናናት
አንድ ፡ ነው ፡ ምንጩ ፡ የበረከት (፪x)
አንድ ፡ ነው ፡ ምንጩ ፡ የበረከት (፪x)
ፍቅርህ ፡ ይጣፍጣል (፫x)
ማራ ፡ የሆነውን ፡ መራራውን
ሕይወት ፡ ያጣፍጣል
ይጣፍጣል ፡ ይጣፍጣል
ፍቅርህ ፡ ይጣፍጣል (፪x)
ደስ ፡ ያለው ፡ ሰው ፡ በአምላኩ ፡ የኮራ
ምን ፡ ያደርጋል ፡ እስኪ ፡ ንገሩኛ
ደስ ፡ ያለው ፡ ሰው ፡ በኢየሱስ ፡ የኮራ
ምን ፡ ያደርጋል ፡ እስኪ ፡ ንገሩኛ
ማመልክ ፡ ነው ፡ እንጂ
ይህንን ፡ ድንቅ ፡ ጌታ (፬x)
ደስ ፡ ያለው ፡ ሰው ፡ በኢየሱስ ፡ የኮራ
ምን ፡ ያደርጋል ፡ እስኪ ፡ ንገሩኛ
ማመልክ ፡ ነው ፡ እንጂ
ይህንን ፡ ድንቅ ፡ ጌታ (፬x)
የማይገርም ፡ ካለ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ጥበብን ፡ አይቶ
አሃሃሃ ፡ አይቶ
ይህ ፡ ህመም ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ ጤንነት ፡ ከቶ
አሃሃሃ ፡ ከቶ
አሥር ፡ ጊዜ ፡ አይኖር ፡ የሚኖረው ፡ አንዴ
አሃሃሃ ፡ አንዴ
ሰው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ኖሮ ፡ ቢሞትስ ፡ ይቆጨዋል ፡ እንዴ
አሃሃሃ ፡ እንዴ
አሥር ፡ ጊዜ ፡ አይኖር ፡ የሚኖረው ፡ አንዴ
አሃሃሃ ፡ አንዴ
ለኢየሱሴ ፡ ኖሬ ፡ ብሞትስ ፡ ይቆጨኛል ፡ እንዴ
አሃሃሃ ፡ እንዴ (፪x)
ለውዴ ፡ አሃሃሃ ፡ ለውዴ (፪x)
ለውዴ ፡ ኦሆሆሆ ፡ ለውዴ
ለውዴ ፡ አሃሃሃ ፡ ለውዴ
|