የዘውትር (Yezewter) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

የፍቅሬ ፡ መሃል ፡ ነህ ፡ የመወደዴም ፡ ቅኔ
አንዳች ፡ አልቆጥብም ፡ አሰማለሁ ፡ እኔ
የመስዋዕቴን ፡ በኩራት ፡ የፍቅሬን ፡ ፍታ
አዘጋጅቻለሁ ፡ ላፈሰው ፡ ለጌታ (፪x)

አዝ፦ ለእኔስ ፡ የዘውትር ፡ ጥማቴ
መሻት ፡ የቀን ፡ የሌሊት ፡ ናፍቆቴ
የአንተን ፡ ክብር ፡ ማየቴ
በዕድሜ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመኔ
በዕድሜ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመኔ (፪x)

የወርቅ ፡ ፍልቃቂ ፡ የክብር ፡ ሙዳዬ
በሞገስ ፡ ያጌጥከው ፡ መጐናፀፊያዬ
የፊቴ ፡ መድኃኒት ፡ የርስቴ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ አላውቅም ፡ የልጅ ፡ ልጅ ፡ ደስታ (፪x)

አዝ፦ ለእኔስ ፡ የዘውትር ፡ ጥማቴ
መሻት ፡ የቀን ፡ የሌሊት ፡ ናፍቆቴ
የአንተን ፡ ክብር ፡ ማየቴ
በዕድሜ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመኔ (፪x)

ከደስታዬ ፡ በላይ ፡ አንተን ፡ ወድጃለሁ
ፅድቅን ፡ መከታተል ፡ ተለማምጃለሁ
ሌላ ፡ ሌላውማ ፡ መች ፡ ልቤ ፡ ደረሰ
የአንተ ፡ ዘይት ፡ ብቻ ፡ ሕይወቴን ፡ አራሰ
ሌላ ፡ ሌላውማ ፡ መች ፡ ልቤ ፡ ደረሰ
የአንተ ፡ ቅባት ፡ ብቻ ፡ አንጀቴን ፡ አራሰ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ የዘውትር ፡ ጥማቴ
መሻት ፡ የቀን ፡ የሌሊት ፡ ናፍቆቴ
የአንተን ፡ ክብር ፡ ማየቴ
በዕድሜ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመኔ (፪x)