From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የቀደስካቸው ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ማምለክ ፡ ስጀምር ፡ ዓይኖቼን ፡ ወደላይ ፡ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
ለሰው ፡ ልጅ ፡ ልማድነቱ
ክብርና ፡ ሞገስ ፡ በሕይወቱ
ለስብዕናውም ፡ ትርጉም
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ አልተገኘም
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ የለም ፡ የለም
አማራጭ ፡ የሌለህ ፡ ምርጫዬ
የሕይወቴ ፡ ገነት ፡ ተድላዬ
ያለ ፡ አንዳች ፡ ቅንጣት ፡ ቅሬታ
ፈቅጄ ፡ የማመልክህ ፡ በደስታ
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አዝ፦ የቀደስካቸው ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ማምለክ ፡ ስጀምር ፡ ዓይኖቼን ፡ ወደላይ ፡ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
አጥንት ፡ ከአጥንት ፡ ሳይዋደድ
ሳልሰራ ፡ በእናቴ ፡ ሆድ
ቀኖቼን ፡ ጽፈህ ፡ በመጽሐፍ
እንደ ፡ ፈቃድህ ፡ እንደ ፡ ሀሳብህ
አራመድከኝ ፡ በትንቢት ፡ ቃልህ
አጋጣሚ ፡ አይደል ፡ ዎይ ፡ በድንገት
የሆንኩትን ፡ ሁሉ ፡ የሆንኩት
የሕይወቴን ፡ አቅጣጫ ፡ ቀያሪ
ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ሆኖ
አንተ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ መርማሬ
አዝ፦ የቀደስካቸው ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ
ማምለክ ፡ ስጀምር ፡ ዓይኖቼን ፡ ወደላይ ፡ አቅንቼ (፪x)
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
ህዋሳቶቼ ፡ አካላቶቼ
አንተን ፡ ይሉኛል ፡ አጥንቶቼ
|