መነሻህ ፡ ከፍታ (Meneshah Kefeta) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

ከሰማሁትና ፡ ይበልጣል
ልዑል ፡ ሆይ ፡ መዓዛህ ፡ ያውዳል
ከመንግስትህ ፡ ህግ ፡ ሁኔታ
መች ፡ ተነገረ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ (፪x)
ከጥበብህ ፡ ህግ ፡ ሁኔታ
መች ፡ ተዘመረ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ
መች ፡ ተዘመረ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ መነሻህ ፡ ከፍታ ፡ መድረሻህ ፡ ከፍታማ
ጅማሬህ ፡ ከፍታ ፡ ፍፃሜህ ፡ ከፍታማ
ዙፋንህን ፡ ዘርግትህ ፡ ከፍ ፡ ባለው ፡ ቦታ
ፀንተህ ፡ ትኖራለህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

ፀንተህ ፡ ትኖራለህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

የምድር ፡ ጠቢባን ፡ ሊቃውንቱ
የፍጥረትን ፡ ጥያቄ ፡ መች ፡ ፈቱ
የጥበብ ፡ የእውቀት ፡ የሥልጣኔ
መጀመሪያው ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ መድህኔ
መጨረሻው ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ መድህኔ (፪x)

ሊቃውንቱ ፡ እንዲህ ፡ ይበሉ
ኃያላኑ ፡ እንዲህ ፡ ይበሉ
ጠቢባኑ ፡ እንዲህ ፡ ይበሉ
ሠራዊቱ ፡ እንዲህ ፡ ይበሉ

ኤልሻዳይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚያብሔር ፡ ብቻ
ኤሎሂም ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ
አዶናይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ብቻ (፰x)

ከምድር ፡ ዳርቻ ፡ እስከ ፡ ጫፍ
ከሠማይም ፡ አፅናፍ ፡ እስከ ፡ አፅናፍ
ከትውልድ ፡ የትውልዶች ፡ መካከል
መች ፡ ተገኘ ፡ አንተን ፡ የሚስተካከል
መች ፡ ተገኘ ፡ አንተን ፡ የሚስተካከል (፪x)

አዝ፦ መነሻህ ፡ ከፍታ ፡ መድረሻህ ፡ ከፍታማ
ጅማሬህ ፡ ከፍታ ፡ ፍፃሜህ ፡ ከፍታማ
ዙፋንህን ፡ ዘርግትህ ፡ ከፍ ፡ ባለው ፡ ቦታ
ፀንተህ ፡ ትኖራለህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

ፀንተህ ፡ ትኖራለህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

ከፍ ፡ ከፍ (፪x) ፡ ብለህ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብለህ
የክብር ፡ የምሥጋናን ፡ ዘውድ ፡ ተጭነህ
በማይናወጠው ፡ ፅኑ ፡ መንግስትህ
ያለ ፡ ተቀናቃኝ ፡ ትገዛናለህ (፪x)

ኤልሻዳይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚያብሔር ፡ ብቻ
ኤሎሂም ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ
አዶናይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ብቻ (፲፮x)