From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ለካ ፡ እግዚአብሔር ፡ እያለ
ለካ ፡ አምላኬ ፡ እያለ (፪x)
አይቆረጥም ፡ ተስፋ
ምኑ ፡ ሁኔታ ፡ ቢከፋ
ኧረ ፡ አይቆረጥም ፡ ተስፋ
ምኑ ፡ ሁኔታ ፡ ቢከፋ
ጥበበኛው ፡ እያለ
ኤልሻዳዩ ፡ እያለ
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ እያለ
ተዓምረኛው ፡ እያለ
አይወራም ፡ ስንፍና
እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነውና
ኧረ ፡ አይወራም ፡ ስንፍና
እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና
እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ገዢ ፡ ነውና
ባይዘንብ ፡ ዝናቡ ፡ ባይነፍስ ፡ ንፋሱ
እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ቀን ፡ አይቀረም ፡ መድረሱ (፪x)
በክብሩ ፡ ማለፊያ ፡ ብሥራውም ፡ ድንቅ
ከአንደበቱ ፡ ቃል ፡ አንዳችም ፡ አይውድቅም
በክብሩ ፡ ማለፊያ ፡ ብሥራውም ፡ ድንቅ
ከአንደበቱ ፡ ቃል ፡ አንዳችም ፡ አይውድቅም
አዝ፦ ለካ ፡ እግዚአብሔር ፡ እያለ
ለካ ፡ አምላኬ ፡ እያለ (፪x)
አይቆረጥም ፡ ተስፋ
ምኑ ፡ ሁኔታ ፡ ቢከፋ
ኧረ ፡ አይቆረጥም ፡ ተስፋ
ምኑ ፡ ሁኔታ ፡ ቢከፋ
ጥበበኛው ፡ እያለ
ኤልሻዳዩ ፡ እያለ
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ እያለ
ተዓምረኛው ፡ እያለ
አይወራም ፡ ስንፍና
እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነውና
ኧረ ፡ አይወራም ፡ ስንፍና
እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ንጉሥ ፡ ነውና
እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነውና
እርሱ ፡ ገዢ ፡ ነውና
የፃድቁ ፡ ጩኸት ፡ መች ፡ በከንቱ ፡ ይቀራል
በትንሳኤው ፡ ማግስት ፡ በድል ፡ ይቀየራል (፪x)
ከፈተናው ፡ ጋራ ፡ መውጫውን ፡ አድርጐ
ሲያመልስ ፡ አይተናል ፡ የሄድውን ፡ ምርኮ
ከፈተናው ፡ ጋራ ፡ መውጫውን ፡ አድርጐ
ሲያመልስ ፡ አይተናል ፡ የሄድውን ፡ ምርኮ
በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ ይበልህ
የልብህን ፡ መሻት ፡ ይሰጥሃል (፪x)
ፅድቁን ፡ መንግስቱን ፡ እሻ
ሁሉ ፡ ይጨመርልሃል (፪x) [1]
ታማኝ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ የሰጠው
በፍፁም ፡ ግድፍ ፡ ጉድለት ፡ የለውም
አደራ ፡ ስጠው ፡ መንገድህን
ያቀናል ፡ ጐዳናህን (፫x)
|
- ↑ ማቴዮስ ፮ ፡ ፴፫ (Matthew 6:33)