ከፍ ፡ አድርጌ (Kef Adregie) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

ከፍ ፡ አድርጌ ፡ መለከቴን ፡ እነፋለሁ
ምሥጋናዬን ፡ አውጃለሁ (፪x)

ከፍጥረታት ፡ ጋር ፡ ተባብሬ
ያለ ፡ የሌለኝን ፡ ጭምሬ
እቀኛለሁ ፡ ለንጉሤ
ጌታ ፡ መጥቷል ፡ በመቅደሴ (፪x)

መድኃኒዓለም ፡ እውነትም ፡ አንተ ፡ እውነትም ፡ መድኃኒት ፡ ነህ
አባትህ ፡ ይህንን ፡ አውቆ ፡ ኢየሱስ ፡ ብሎህ ፡ ጠራህ
የባህሩ ፡ ምሳሌ ፡ የክብሩ ፡ ነፀብራቁ ፡ ነህ
የእኔንም ፡ ሕይወት ፡ ያደመቅህ ፡ የደስታዬ ፡ ፍፃሜው ፡ ነህ

ጌታዬ ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ
የዘላለም ፡ መኖሪያዬ
አምላክ ፡ የምለው ፡ አንተን ፡ ነው
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ፡ ተቀበለው
ወዳጅ ፡ የምለው ፡ አንተን ፡ ነው
ምሥጋናዬን ፡ ተቀበለው (፪x)

ረዳት ፡ የምለው ፡ አንተን ፡ ነው
ምሥጋናዬን ፡ ተቀበለው

እያደር ፡ እያደር ፡ ዛሬማ ፡ እያደረ
ይገረመኝ ፡ ጀመረ ፡ የመዳኔ ፡ ነገር
እያደር ፡ እያደር ፡ ዛሬማ ፡ እያደረ
ይደንቀኝ ፡ ጀመረ ፡ የመዳኔ ፡ ነገር
ለካ ፡ ድኛለሁ ፡ ከሞት ፡ አምልጬ
የጠላቶችን ፡ እራስ ፡ ረግጬ (፪x)

የሚያስደንቅ ፡ ነው ፡ መዳኔ
እንደበራለኝ ፡ ለእኔ
ኢየሱሴ ፡ ሆነልኝ
ማንም ፡ የማይወስድብኝ

መዳኔ ፡ ድንቅ ፡ ነው
መዳኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x)

ከፍ ፡ አድርጌ ፡ መለከቴን ፡ እነፋለሁ
ምሥጋናዬን ፡ አውጃለሁ (፪x)

ከፍጥረታት ፡ ጋር ፡ ተባብሬ
ያለ ፡ የሌለኝን ፡ ጭምሬ
እቀኛለሁ ፡ ለንጉሤ
ጌታ ፡ መጥቷል ፡ በመቅደሴ (፪x)