From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ እኔማ ፡ ቢሆንልኝማ
በክብርህ ፡ ውስጥ ፡ አድሬ
በህልውናህ ፡ ኖሬ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ፈትህን
ታይቶ ፡ የማይጠገበውን
ካገኘሁ ፡ ያኔ ፡ ኖርኩኝ/ረካሁ ፡ እላለሁ (፪x)
ፍፁም ፡ እንከን ፡ የሌው ፡ ውብትህ
ደናግሎች ፡ አይተው ፡ ወደድዱህ (፪x)
ሳበኝ ፡ እሮጣለሁ ፡ ከኋልህ
ሳይህ ፡ ውዬ ፡ ባድር ፡ አልጠግብህ
ሳይህ ፡ ውዬ ፡ ባድር ፡ አልጠግብህ (፪x)
አልጠግብህ (፮x)
አልጠግብህ ፡ ጌታ ፡ አልጠግብህ
የዕድሜ ፡ ልክ ፡ ፍስሃ ፡ በቀኝህ
የሚያበራ ፡ ፀዳል ፡ ስላለህ (፪x)
ፃድቅ ፡ በብርሃንህ ፡ ይራመዳል
ከህልውናህ ፡ ውጭ ፡ የት ፡ ይኬዳል (፪x)
አዝ፦ እኔማ ፡ ቢሆንልኝማ
በክብርህ ፡ ውስጥ ፡ አድሬ
በህልውናህ ፡ ኖሬ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ፈትህን
ታይቶ ፡ የማይጠገበውን
ካገኘሁ ፡ ያኔ ፡ ኖርኩኝ/ረካሁ ፡ እላለሁ (፪x)
የተትረፈረፈ ፡ ነው ፡ ፅዋዬ
ከአምላክ ፡ ፊት ፡ ሆኖልኝ ፡ ገበታዬ (፪x)
የንጉሥ ፡ ማዕረግ ፡ ለምዳለች ፡ ነፍሴ
ተጣብቃልኝ ፡ በኢየሱሴ (፪x)
በኢየሱሴ (፰x)
|