ኢየሱሴ (Eyesusie) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

በምሥጋና ፡ አከብርሃለሁ
በዝማሬ ፡ አደንቅሃለሁ (፪x)
ኢየሱሴ ፡ ወድጄሃለሁ
ኢየሱሴ ፡ አፍቅሬሃለሁ

አዝኢየሱሴ (፪x) ፡ መታመኛዋ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ መደገፊያዋ ፡ ለነፍሴ (፪x)

ልባርክ ፡ ነው ፡ ብለህ ፡ ሳታማክራቸው
ላስደንቅ ፡ ነው ፡ ብለህ ፡ ሳታማክራቸው (፪x)

ፍፁም ፡ ሳይጠብቁ ፡ ፍንጭን ፡ ሳትሰጣቸው
አቤት ፡ ጠላቶቼን ፡ ጉድ ፡ አደረካችው (፪x)

ጉድ ፡ አደረካቸው (፬x)

አዝኢየሱሴ (፪x) ፡ መታመኛዋ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ መደገፊያዋ ፡ ለነፍሴ (፪x)

ከፊተኛው ፡ ይልቅ ፡ እንዲሻል ፡ ኋለኛው
ተናገረህ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ ጌታ ፡ ጥበበኛው (፪x)

አዲስ ፡ የወይን ፡ ጠጅ ፡ በአዲስ ፡ አቁማዳ
ታናኳዬን ፡ ሞላኸው ፡ በበረከት ፡ ናዳ (፪x)

በበረከት ፡ ናዳ (፬x)

አዝኢየሱሴ (፪x) ፡ መታመኛዋ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ መደገፊያዋ ፡ ለነፍሴ (፪x)

ቀንበር ፡ የሚሰብር ፡ የቅባት ፡ ውፍረት
ሕይወትን ፡ የሚያድስ ፡ የፀጋ ፡ ሙላት (፪x)

የበረከት ፡ ዝናብ ፡ ውሽንፍር ፡ ሲመጣ
አልዋለ ፡ አላደረም ፡ ፋሬስ ፡ ጥሶ ፡ ወጣ (፪x)

ፋሬስ ፡ ጥሶ ፡ ወጣ (፬x)

አዝኢየሱሴ (፪x) ፡ መታመኛዋ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ (፪x) ፡ መደገፊያዋ ፡ ለነፍሴ (፪x)