እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ (Erasu New Gieta) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

ከዕንቁና ፡ ከብዙ ፡ ወርቅ
የምትበልጥብኝ ፡ የእኔ ፡ እፁብ ፡ ድንቅ
እህል ፡ ውኃዬ ፡ የእኔ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ
መጓደጃዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ አሃ
እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው (፪x)

የሞገስ ፡ አክሊል ፡ የክብር ፡ ሹመቴ
የማዕረግ ፡ ዘንግ ፡ ሆነህ ፡ ለሕይወቴ
ገመድ ፡ ባማረ ፡ ሥፍራ ፡ ወድቃለች
በአንተ ፡ በአምላኬ ፡ ርስቴም ፡ ተዋበች

የእኔ ፡ ትርጉም ፡ በረከት ፡ ማለት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ አሃ ፡ የሕይወት ፡ ምንነት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ ባለ ፡ ጠግነት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ አሃ ፡ የኑሮ ፡ ስኬት

ከምንም ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ በላይ
እራሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)

አዝ፦ እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ አሃ
እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው (፪x)

በእጁ ፡ መነካት ፡ ተነክቼአለሁ
የክብሩን ፡ ውበት ፡ በዓይኔ ፡ አይቻለህ
በደረስኩበት ፡ በሁሉም ፡ ቦታ
እናገራለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ (፪x)

የእኔ ፡ ትርጉም ፡ በረከት ፡ ማለት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ አሃ ፡ የሕይወት ፡ ምንነት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ ባለ ፡ ጠግነት
የእኔ ፡ ትርጉም ፡ አሃ ፡ የኑሮ ፡ ስኬት

ከምንም ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ በላይ
እራሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x)

አዝ፦ እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ አሃ
እራሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እራሱ ፡ ነው (፬x)