አመልክሃለሁ (Amelkehalehu) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg


(3)

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ
(Yenardos Shetoyie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ
እገዛልሃለሁ ፡ በደስታ (፪x)

ብዙ ፡ ምርኮን ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው
እኔም ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ተሰኘሁ (፪x)

እወድሃለሁ ፡ ብልህ ፡ መች ፡ ይገልፅልኛል
አፈቅርሃለሁ ፡ ብልህ ፡ መች ፡ ይገልፅልኛል
ምድራዊው ፡ ቃል ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ አንሶብኛል
ግን ፡ ደግነቱ ፡ አንተ ፡ መች ፡ ቃል ፡ ትቆጥራለህ
ይልቅ ፡ የውስጥ ፡ የልብን ፡ መመዝን ፡ ታዋቃለህ (፪x)

እንደ ፡ ወንዝ ፡ እንደ ፡ ጅረት
እንደሚጠጣ ፡ ገነት (፪x)

የፅድቅ ፡ ብዛት ፡ የአንተ ፡ ፀጋ
የተጠማችን ፡ ነፍስ ፡ የሚያረካ (፪x)

የሕይወትን ፡ ጥም ፡ የሚያረካ (፬x)

አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ጌታ
እገዛልሃለሁ ፡ በደስታ (፪x)

ብዙ ፡ ምርኮን ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው
እኔም ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ተሰኘሁ (፪x)

የምህረትህ ፡ ጥገኛ
የፍቅርህ ፡ ድግሞ ፡ እስረኛ (፪x)

ከአንተ ፡ ውጭ ፡ የለኝም ፡ ማንነት
ላፍሰው ፡ ልቤን ፡ በአንተ ፡ ፊት
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ የለኝም ፡ ማንነት
ላፍሰው ፡ ልቤን ፡ በአንተ ፡ ፊት (፮x)