ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል (Feqreh Nektognal) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lyrics.jpg


(2)

መዓዛህን ፡ እወደዋለሁ
(Meazahen Ewedewalehu)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የለዓለም ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Lealem Tilahun)

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ
እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ አየቼ ፡ ማላውቀው
እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ በልጁ ፡ የገለጸው
በአስደናቂው ፡ ፍቅርህ ፡ የባረካት ፡ ነፍሴ
እጀግ ፡ ወዳሃለች ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱሴ

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ
እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

የተወደደች ፡ ቀን ፡ አንተን ፡ ያወኩባት
እንደምን ፡ ያቺ ፡ ዕለት ፡ የተባረከች ፡ ናት
መደነቄ ፡ በዝቷል ፡ ካወኩህ ፡ ጀምሮ
ይቆጨኝ ፡ ነበረ ፡ ያንተ ፡ ባልሆን ፡ ኖሮ

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ
እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)

በፊትህ ፡ ደስታ ፡ በመገኘትህ
ደስ ፡ የምታሰኘኝ ፡ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ
የፍቅር ፡ ትርጉሙ ፡ የገባኝ ፡ ባንተ ፡ ነው
ከማመስገን ፡ በቀር ፡ የምልህ ፡ ምንድን ፡ ነው

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ነክቶኛል ፡ ምን ፡ አረጋለሁ
እጄን ፡ ዘርግቼ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)