Lealem Tilahun/Hailenem Yemiyastateqegn/Medanie Sigermegn
ርዕስ መዳኔ ሲገርመኝ ዘማሪ ለዓለም ጥላሁን አልበም ኃይልንም የሚያስታጥቀኝ
መዳኔ ሲገርመኝ አይኔ መከፈቱ ደግሞ ታምራትህ በዛ በየእለቱ (፪x) አንተን አመስግኜ ማቋረጥ አልችልም ውስጤ የገባው ፍቅርህ ዝም አያሰኘኝም ዝም አያሰኘኝም (፪x)
አዝ ዓይኖቼንም እያበራህ ጉልበቴንም እያጸናህ ወደ ፊት እያራመድከኝ በድል ላይ ድልን ሰጠኅኝ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ (፪x)
መዘመር ለአንተ ነው ማምለክም አንተን ድንቅን እየሰራህ ለምታኖረን (፪x) እንዲያው ክበር እንጂ ሌላ ምን ይባላል ጌታ ያንተ ፍቅር ከመታወቅ ያልፋል ከመታወቅ ያልፋል (፪x)
አዝ ዓይኖቼንም እያበራህ ጉልበቴንም እያጸናህ ወደ ፊት እያራመድከኝ በድል ላይ ድልን ሰጠኅኝ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ (፪x)
አንተው በሰጠህኝ በዚች አንደበቴ እባርክሃለሁ ክበር መድኃኒቴ (፪x) ከልብ የፈለቀ የምስጋና ዜማ ይሄው አምጥቻለሁ በፊትህ ላሰማ በፊትህ ላሰማ (፪x)
አዝ ዓይኖቼንም እያበራህ ጉልበቴንም እያጸናህ ወደ ፊት እያራመድከኝ በድል ላይ ድልን ሰጠኅኝ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ (፪x)
መዳኔ ሲገርመኝ አይኔ መከፈቱ ደግሞ ታምራትህ በዛ በየእለቱ (፪x) አንተን አመስግኜ ማቋረጥ አልችልም ውስጤ የገባው ፍቅርህ ዝም አያሰኘኝም (፪x)
መዘመር ለአንተ ነው ማምለክም አንተን ድንቅን እየሰራህ ለምታኖረን (፪x) እንዲያው ክበር እንጂ ሌላ ምን ይባላል ጌታ ያንተ ፍቅር ከመታወቅ ያልፋል ከመታወቅ ያልፋል። (፪x)
አዝ ዓይኖቼንም እያበራህ ጉልበቴንም እያጸናህ ወደ ፊት እያራመድከኝ በድል ላይ ድልን ሰጠኅኝ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ