From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- ተናግሬም ፡ አልጨርሰው ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው (፪x)
ልነሳና ፡ እስኪ ፡ ልቀኝ ፡ ለእርሱ ፡ ሚሆን ፡ ቋንቋ ፡ ቢገኝ (፪x)
ዝም ፡ ልል ፡ አልችልም
ፍቅርህ ፡ ዝም ፡ አያሰኝም
ጥበቃህና ፡ ምሕረትህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
መውደድህ (፪x)
ለመጠሩት ፡ ሁሉ ፡ ባለ ፡ ጠጋ
ከወንድም ፡ አብልጦ ፡ የሚጠጋ
ከማንስ ፡ ጋር ፡ ከቶ ፡ ይወዳደራል
ከአእላፋት ፡ ይልቅ ፡ እርሱ/ጌታ ፡ ይበልጣል (፪x)
አዝ:- ተናግሬም ፡ አልጨርሰው ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው (፪x)
ልነሳና ፡ እስኪ ፡ ልቀኝ ፡ ለእርሱ ፡ ሚሆን ፡ ቋንቋ ፡ ቢገኝ (፪x)
ዝም ፡ ልል ፡ አልችልም
ፍቅርህ ፡ ዝም ፡ አያሰኝም
ጥበቃህና ፡ ምሕረትህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
መውደድህ (፪x)
ከቤቱ ፡ በረከት ፡ የሚያጠግበን
የዘላለም ፡ አባት ፡ የማይተወን
ጎልማስነታችን ፡ ደስ ፡ የምያሰኛት
ውዱ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ የእኛ ፡ መድሃኒት (፪x)
አዝ:- ተናግሬም ፡ አልጨርሰው ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው (፪x)
ልነሳና ፡ እስኪ ፡ ልቀኝ ፡ ለእርሱ ፡ ሚሆን ፡ ቋንቋ ፡ ቢገኝ (፪x)
ዝም ፡ ልል ፡ አልችልም
ፍቅርህ ፡ ዝም ፡ አያሰኝም
ጥበቃህ ፡ ምሕረትህ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
መውደድህ (፪x)
|