From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
ንጉሴ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው ፡ አምባዬ (፪x)
አዝ:- ኃይልንም ፡ የሚያስታጥቀኝ
ቅጥሩንም ፡ የምያዘልለኝ
እግሮቼን ፡ የሚያበረታ
የሚያቆመኝ ፡ በከፍታ (፪x)
ዛሬ ፡ ታሪኬ ፡ ተለውጧል
ጠላት ፡ እያየ ፡ ይቃጠላል ፡ አሀ
ጌታ ፡ ሰጥቶኛል ፡ መሻቴን
ዘይት ፡ ቀብቶ ፡ እራሴን (፪x)
በክብር ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ክብር ፡ በክብር ፡ ላይ ፡ አሃ
ቆርጫለሁ ፡ ለመጨመር ፡ ከዚያም ፡ በላይ
አንደበቴን ፡ በምስጋና ፡ እየከፈትኩ ፡ ኦሆ
ለድል ፡ ጌታ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አመጣለሁ
አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
ንጉሴ ፡ መደገፊያዬ ፡ ነው ፡ አምባዬ (፪x)
አዝ:- ኃይልንም ፡ የሚያስታጥቀኝ
ቅጥሩንም ፡ የምያዘልለኝ
እግሮቼን ፡ የሚያበረታ
የሚያቆመኝ ፡ በከፍታ (፪x)
እግሮቼን ፡ የሚያበረታ
የሚያቆመኝ ፡ በከፍታ (፫x)
|